የመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊነት

(ከሀሣዊ ፊሎ የተዛወረ)

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊነት (ሮማይስጥ፦ Liber Antiquitatum Biblicarum /ሊቤር አንቲኲታቱም ቢብሊካሩም/ ወይም «የመጽሐፍ ቅዱስ ቅርሶች») በጥንት የተቀነባበረ የአይሁዶች ታሪክ መጽሐፍ ነው።

አሁን ጽሑፉ የሚታወቀው በሮማይስጥ ትርጉም ብቻ ሲሆን ፣ ከጥንታዊ አይሁዳዊው ፈላስፋ ፊሎ (28 አክልበ.-42 ዓም ገደማ) ጽሑፎች ጋር አብሮ ተገኝቶ ስለ ደረሰልን፣ ለረጅም ጊዜ ፊሎ እራሱ የጻፈ ድርሰት እንደ ነበር ታሰበ። ዛሬ በፊሎ እንደተጻፈ ስለማይታመን፣ መጽሐፉ «ሲውዶ ፊሎ» (Pseudo-Philo ወይም «ሐሣዊ ፊሎ» በመባል ይታወቃል። በጽሁፉ ውስጥ የደራሲው ስም መቸም ስለማይጠቀስ፣ ይዘቱ ሆን ብሎ በሐሠት ተጽፏል ለማለት ሳይሆን፣ ፊሎ በውነት እንዳልጻፈው ብቻ ለማመልከት ነው «ሐሣዊ ፊሎ» የተባለው።

ታሪኩ በተጻፈበት ወቅት የአይሁዶች ዋና ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ገና እንዳልጠፋ ይመስላል፤ ስለዚህ ብዙዎቹ ሊቃውንት ከ62 ዓም አስቀድሞ እንደ ተቀነባበረ ገመቱ። የተጻፈበት ቋንቋ ዕብራይስጥ ሲሆን ከዚያ ወደ ግሪክኛ፣ ከዚያም ከግሪክኛ ወደ ሮማይስጥ እንደ ተተረጎመ ይታስባል። በዚህ መንገድ በይዘቱ ውስጥ ካሉት ስያሜዎች በሮማይስጥ ሲነበቡ በርካታዎች ከዕውቅና መጠን ይልቅ ተዛብተዋል።

ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ያሉትን ታሪኮች ከአዳም ጀምሮ እስከ ንጉሥ ሳኦል ዕረፍት ዘመን (እስከ 1008 ዓክልበ. ግድም) ድረስ ያወራል። የተጻፈው እንኳ ከረቢ አኪቫ በን ዮሴፍ ማሶራዊ ትርጉም አስቀድሞ በመሆኑ፣ ለታሪካዊ አስተያየቶቹ ጥቂት ዋጋ ያለው መጽሐፍ ይቆጠራል። ሆኖም ከምናውቀው መጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በብዙ ረገዶች ይለያል ወይም ተጨማሪ መረጃ አለው።

ከመጀመርያው የአዳምና የሕይዋን ወንድና ሴት ልጆች ስሞች ሁሉ ይዘርዝራል፣ እንዲሁም የሴት፣ የሔኖስ፣ ወዘተ. እስከ ኖኅ ድረስ፣ ወንድና ሴት ልጆቻቸው ስሞች ሁሉ ይዘረዘራሉ፣ እንዲሁም የኖህ ልጅ ልጆች የዘርዘራሉ። ተመሳሳይ መረጃ እንደገና በኋላ በተጻፉት የአይሁዶች መጻሕፍት (በተለይ የየራሕሜል ዜና መዋዕል) ውስጥ ደግሞ ይገኛል።

የባቢሎን ግንብ ታሪክ ሲያወራ፣ ግንቡን ከማገንባት እምቢ ካሉት ሰዎች መካከል አብራም (አብርሐም) ይቆጠራል። ይህ በኦሪት ዘፍጥረት ወይም በመጽሐፈ ኩፋሌ ቅደም ተከተል ባይቻልም፣ አብርሃም በናምሩድ ዘመን ኖረ የሚለው ታሪክ ግን በተልሙድና በሌሎች አይሁድ መጻሕፍት ብዙ ጊዜ ይታያል።

በተለይ ከኢያሱ ወልደ ነዌ ቀጥሎ ቄኔዝዜቡል የተባሉት ፈራጆች በእስራኤል ላይ ለ82 ዓመታት እንደ ፈረዱ በአንዳንድ ምዕራፍ ይገልጻል። በብሉይ ኪዳን ይህን ሳይጠቀስ በቀጥታ ወደ አራም-ናሐራይም ንጉሥ ኲሰርሰቴም ባዕድ ገዥነት ይዘልላል። በ«ሐሣዊ ፊሎ» ግን ከዜቡል በኋላ ቀጥታ ወደ ኢያቢስባራክዲቦራ ይዘልላልና የኲሰርሰቴም፣ ጎቶንያልኤግሎም ወይም ናዖድን ዘመናት አይጠቅሳቸውም።