ለውረን ዳይጎል

አሜሪካዊ ዘፋኝ እና ዘፋኝ
(ከLauren Ashley Daigle የተዛወረ)

ለውረን አሽሊ ዳይጎል (ላቲን Lauren Ashley Daigle) (የተወለዱት እ.ኤ.አ መስከረም 9፣ 1991 ዓ.ም ነው)[1][2] የአሜሪካ ዘመናዊ የክርስቲያን ሙዚቃ ዘማሪና እና የዜማ ደራሲ ናቸው። ወደ ሴንትሪሲቲ ሙዚቃ ከተሰየሙ በኋላ "ኻው ከን ኢት ብ" የተባለውን የመጀመሪያ አልበማቸውን እ.ኤ.አ በ2015 አወጡ። መዝሙሩም በቢልቦርድ ከፍተኛ የክርስቲያን አልበሞች ገበታ ላይ ቁጥር 1 ሆኗል፣ በአር.አይ.ኤ.ኤ(RIAA) ፕላቲነም የምስክር ወረቀት ያስገኘ ሲሆን ክርስቲያናዊ ኤርፕለይ ቢልቦርድ ገበታ ላይ የመጀመሪያ የሆኑትን ሌሎች ነጠላ ዜማዎችንም አፍርቷል፤ እነርሱም ፌርስትትረስት ኢን ዩ እና ኦ ሎርድ ናቸው።

ላውረን ዳይጎል በ 2023ኙ ኮንሰርት ላይ

የዳይጎል ሦስተኛው የስቱዲዮ አልበም የሆነው “ሉክ አፕ” በመስከረም ወር 2018 ተለቋል። ይህም “ዩ ሰይ” በሚለው ነጠላ ዜማ የፖፕ ክሮስ-ኦቨር ስኬት አመጣና በቢልቦርዱ 200 ዝርዝር ውስጥ ሦስተኛ ሊሆን ቻለ። በተጨማሪም ከ 20 ዓመት በላይ ሴቶች ምድብ በብዛት የተሸጠ የክርስቲያን አልበም የተባለ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ወደ 115 ሺህ የሚጠጋ ጊዜ በመሸጥ በብዛት የተሸጠ የክርስቲያን አልበም ለመሆንም በቅቷል። [3] የአልበሙ መሪ ነጠላ ዜማ የሆነው "ዩ ሰይ" በብዛት የተሸጠ በሚል በቢልቦርድ 100 ስር 29ኛ ደረጃ የያዘ ሲሆን ለ101 ሳምንታት በቢልቦርድ "ሆት ክርስቲያን ሶንግ" ቻርት ላይ አንደኛነቱን አስጠብቋል። አልበሙና ነጠላ ዜማው ዳይጎልን ለግራሚ አዋርድስ አብቅቷቸዋል።

የልጅነት ጊዜያቸው

ለማስተካከል

ዳይጎል የተወለዱት በሌክ ቻርልስ ሉዊዚያና ውስጥ ሲሆን እድገታቸው ደግሞ የሉዊዚያና ግዛት ላፋዬቴ ነው። በአካባቢያቸው ዚዴኮብሉዝ እና ካጁን ሙዚቃ ተጽዕኖ አድርጎባቸዋል።[4][5] ሁለ ከመዘመራቸው የተነሳ እናታቸው የሙዚቃ ሳጥን ይሏቸው ነበር።[6][7]

  1. ^ "Getting to Know Lauren Daigle – KGEB" (በen-US).
  2. ^ "Lauren Daigle on Apple Music" (በen-gb).
  3. ^ Caulfield, Keith (September 16, 2018). "Paul McCartney Earns First No. 1 Album in Over 36 Years on Billboard 200 Chart With 'Egypt Station'". Billboard. በSeptember 17, 2018 የተወሰደ.
  4. ^ Daigle, Lauren Ashley. "Lauren Ashley Daigle". SESAC. በJanuary 16, 2015 የተወሰደ.
  5. ^ "About Lauren Daigle". MTV. Archived from the original on December 15, 2016. በNovember 17, 2014 የተወሰደ.
  6. ^ "Lauren Daigle on K-LOVE".
  7. ^ How Lauren Daigle Is 'Bringing People Together' Through Her New Archived ሜይ 1, 2021 at the Wayback Machine 'Hold on to Me' Music Video (May 1, 2021)