ዓ.ም.
የምዕራብ የቀን መቁጠሪያ ዘመን
ዓመተ ምሕረት ከኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ አለም መምጣት ጋር ተያይዞ በአብዘኛው ክርስቲያናዊ ማሕበረሰብ ዘንድ ለዘመን መግለጫነት ወይም መጠሪያነት የሚሰጥ ስያሜ ነው።
ስያሜ
ለማስተካከልበመካከለኛው ዘመን ላቲንኛ ዐኖ ዶምኒ (AD) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜው ዘመነ ጌታ ወይም የጌታችን ዘመን የሚል ነው፤ ይህም የተወሰደው "ዐኒ ዶምኒ ኖስትሪ ጄሱ ክርስቲ" (በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን) ከተሰኘ ላቲን ኃይለ ቃል ነው።[1] በኢትዮጵያም ለዚሁ በቀረበ መልኩ ዓመተ ምሕረት በመባል ተተርጉሟል። አንዳንድ ጊዜ ሰኩለር ለማድረግ ስፈልጉ የተለያዩ ፀሐፍት ከ፲፯ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ የጋራ ዘመን ወይም ኮሜን ኢራ(ሲ.ኢ) በማለት የመጻፍ የጀመሩ ቢሆንም እንደምክንያትነት የሚወሰደው ነገር የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መምጣት እንድሆነ ይታምናል።[2]