የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

F / fላቲን አልፋቤት ስድስተኛው ፊደል ነው።

Latin alphabet Ff.svg
ግብፅኛ
ሐጅ
ቅድመ ሴማዊ
ዋው
የፊንቄ ጽሕፈት
ዋው
የግሪክ ጽሕፈት
ዲጋማ
ኤትሩስካዊ
F
ላቲን
F
T3
Proto-semiticW-01.png PhoenicianW-01.svg Digamma uc lc.svg EtruscanF-01.svg RomanF-01.png

የ«F» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዋው» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበትር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።

በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ድምጽ እንደ ተናባቢ («ው») ሲሆን በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ምልክት የአናባቢ ድምጽ «ኢው» (Υ, υ) ለማመልከት ተጠቀመ። ቅርጹ ትንሽ ተለውጦ ግን ተነባቢውን «ው» ለማመልከት Ϝ ϝ («ዋው» ወይም «ዲጋማ») ተጠቀመ። ከዚህ በኋላ «ው» የሚለው ተነባቢ ከግሪክኛ አነጋገር ስለ ጠፋ፣ «Ϝ ϝ» ለቁጥር (፮) ብቻ ሆነ። (ደግሞ ስቲግማ ይዩ።)

ኤትሩስክኛ ደግሞ «F» ለተነባቢው «ው» ይወክል ነበር። የ«ፍ» ድምጽ ለመወክል «FH» ተጻፈ። በሮማይስጥ ሌላ ምልክት «V» ለ«ው» ስለ ተጠቀመ፣ በላቲን ፊደል ፊደሉ «F» ለ«ፍ» ሊወክል ጀመር።

ግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ወ» («ዋዌ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ዋው» ስለ መጣ፣ የላቲን 'F' ዘመድ ሊባል ይችላል። እንዲሁም የላቲን UVW፣ እና Y ሁሉ ከ«ዋው» ደረሱ።

Commons-logo.svg
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ F የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።