ፕሮሶፒስ (Prosopis) የዛፍ ወገን ሲሆን ለመካከለኛ አሜሪካና ለደቡብ አሜሪካ የተፈጥሮ ኗሪዎች ናቸው። በአለም ዙሪያ ግን በብዙ አገራት ወራሪ አረሞች ሆነዋል።

ወራሪ ፕሮሶፒስ ጫካ በሕንድ አገር
የማር መስኪት ዝምቡጥ አተር

የፕሮሶፒስ ዛፎች ማለፊያ እንጨት ይሰጣሉ፤ ከዛፉም አተር ወይም ዝምቡጥ እንደ ስንዴ የሚጠቀም የመስኪት ዱቄት ሊሠራ ይቻላል።

ሆኖም ተክሉ በፍጥነት ስለሚስፋፋ፣ ሌሎችን ዝርዮች ስለሚከለክል፣ እጅግ በጣም ጥልቅና ትልቅ የሆኑት ሥሮች ስላሉት፣ ቢምቢ እና አራዊት ስለሚኖሩበት፣ ብዙ የፕሮሶፒስ ዝርዮች በተለይም P. juniflora (ተራ መስኪት) እና P. glandulosa (የማር መስኪት) አስቸጋሪ ናቸው። በተለይ በኢትዮጵያ አፋር ክልል ወራሪዎች ሲሆኑ እንዲሁም በአውስትራሊያሃዋኢስሪ ላንካጃማይካኬንያሕንድናይጄሪያሱዳንሶማሊያሴኔጋልደቡብ አፍሪካ የፕሮሶፒስ ችግር አለ።

«መስኪት» የሚለው ስያሜ (እንግሊዝኛ፦ mesquite) የደረሰው ከእስፓንኛ /መዝኪቴ/፣ ከናዋትል /ሚዝኪትል/ ነበር። ዛፎቹም በአለም ዙሪያ በብዙ ሌሎች ስሞች ይባላሉ።

ሥሮቹ እስከ 20 ወይም 30 ሳንቲ ሜትር ጥልቀት ድረስ ካልተሰበሩ ተክሉ ይመልሳል፣ ስለዚህ ማጥፋቱ ቀላል አይደለም።