ፔትሮሊየም ወይም ክሩድ ዘይት በተፈጥሮ ከመሬት በታች የሚገኝ የተቀጣጣይነት ጸባይ ያለው ፈሳሽ ነው። የተገነባው ከውስብስብ የሀይድሮካርቦን እና ሌሎች ውህዶች ጥምረት ነው።

የ«ክሩድ» (እንግሊዝኛ፦ crude ማለት «ጥሬ») ዘይት (የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት) በዓለም ውስጥ በብዛት የሚገዛና የሚሸጥ ፤ ጠቀሜታውም ከሃምሳ በመቶ በላይ የሆነውን በዓለም ላይ የሚገኝ የቤትና የመስሪያ ቤት፣ የፋብሪካና የማምረቻ ቦታዎችን፣ እንዲሁም የመንቀሳቀሻና የመጓጓዣ ንብረቶችን እንዲሠሩ የሚያደርግ ልዩ የተፈጥሮ የማዕድን ዘይት ነው። ከነዚህም የተለያዩ ግልጋሎቶች መካከል ፤ እንደየተጥቃሚው ፍላጎት ፣ከምግብ ማብሰያ ኬሮሲን እስከ መኪና ቤንዚን እና የጭነት መኪና ናፍጣ እንዲሁም የአውሮፕላን ማብረሪያ ልዩ ቤንዚን፣ የሞተር ዘይትና የፋብሪካ ማሺን ማንቀሳቀሻ ጠቀሜታው ያለውና ተፈላጊነትም ለሁልጊዜ ያለው ነው።

ክሩድ ዘይት ከመሬት ውስጥ ሲወጣ የተለያየ አይነት ጥራት ይዞ ነው የሚገኘው ። ክሩድ ዘይትን ከኮሞዲቲ መለዋወጫ ቦታ ላይ ለመግዛት በሚፈለግበት ጊዜ የጥራቱን ዓይነት በስሙ ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ምክንያቱም የዋጋው ሁኔታ በዘይቱ ጥራት ይለያያል። ይህ ክሩድ ዘይት በሁለት የመለያያ ዘዴዎች ይመደባል።

አንደኛው ላይት ኤንድ ስዊት ፤ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሄቪይ ኤንድ ሳዎር ይባላል።

ስሙ በእንግሊዘኛ ሲሆን የሚነገደውም በዚሁ ስም ነው - የመገበያያው ስም (በሲምቦል (የአብሪቬሽን)) ስም ቢኖረውም ሁሉንም በእንግሊዘኛው ቃላት ማንበብ ስለ ክሩድ ዘይቱ አነጋገድ ሁኔታ ለማስታወስ ይቀላል።

የክሩድ ዘይት በሁለት ዓይነት የጥራት ልዩነት መደብ የተደረገበት ዋንኛው ምክንያት የዘይቱ ውፍረትና የሠልፈር ፐርሰንት መጠን በመለያየቱ የተለየ ስለሆነ ነው። የዘይቱ ወፍራምነት ዘይቱ በምን ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስረዳ ሲሆን በሚወፍርበት ወይም በሚቀጥንበት ጊዜ የመገልገያና የመጠቀሚያ ሞተሮች ከመኪና ጀምሮ እስከ አውሮፕላን ፣የቤት ወይም የመስሪያ ቤት ተጠቃሚዎች፣ የፋብሪካና የምርት መሣርያ መጠቀሚያዎች ፍላጎት ከነዚህ ሁለት (ላይት ኤንድ ስዊት ክሩድ ዘይት ወይንም ሄቪይ ኤንድ ሳዎር ክሩድ ዘይት) ጥራት መደብ ይነት አይለይም።

እንደዙሁም ሠልፈር መጠን የአንደኛው መለያ የሆነበት ዘይቱ ምን ያክል አሲድ እንዳለውና የዘይቱን ንፅህና ይገልፃል። በዚህም ምክንያት ብዙ ሠልፈር ያልው ሳዎር ክሩድ ዘይት ሲባል አነስተኛ ሠልፈር ያልው ደግሞ ስዊት ክሩድ ዘይት ይባላል።

የክሩድ ዘይት አይነቶች እነዚህ ናቸው፦

  • ሳዎር ክሩድ ኦይል
  • ስዊት ክሩድ ኦይል እና
  • ብሌንድ ስቶክ (የክሩድ ዘይቱን ሠልፈር መጠን ለማስተካከል የነዳጅ አምራች አግሮች ያደባለቁት ነው)


የተጣራ ነዳጅ ዘይት አይነቶች እነዚህ ናቸው፦

የተጣራ ዘይት ምርት ውጤቶች ወይንም ሪፋይንድ ክሩድ ኦይል መደብ ውስጥ የሚገኙና በገበያ ላይ የዋጋ ልዪነት በየጊዜው የሚያሳዩ፣ ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ የሚያጓጉ ከዚህ በታች ይገኛሉ።

  • ጋዞሊን - ቤንዚን
  • ሂቲንግ ኦይል - የማሞቂያ የማብሰያ ጋዝ
  • ዲዝል - ናፍጣ
  • ኬሮሲን - የኩራዝ ጋዝ
  • አውቶሞቢል ሉብሪኬቲንግ ኦይል - የመኪና ሞተር ዘይት
  • ፕሮፔይን - ቡቴን ጋዝ
  • ፔትሮኬሚካል - ከዘይት የሚገኙና ክተለያዩ የዘይት ዓይነቶርች ጋር ለመቀመሚያና መደባለቂያ የሚያስችሉ የዘይት ክፍሎች
  • አስፋልት - የመንገድ መስሪያ ሬንጅ


የድፍድፍ ዘይት ይሚለካው በ ባሬል ( ጉርድ በርሚል በሚመስል) መያዣ ሲሆን ፤ አንድ ባሬል ክሩድ ዘይት አርባ ሁለት ጋሎን ወይንም አንድ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሊትር ነው። በኮሞዲቲ ገበያ ላይ ሲሸጥም በ ሲ.ኤል. (CL) ስም ነው።