ፓንዲዳክቴሪዮን
የጠፋው የምስራቅ ሮም ዩኒቨርሲቲ
(ከፓንዲዳክታሪዮን የተዛወረ)
ፓንዲዳክቴሪዮን በቁስጥንጥንያ፣ ቢዛንታይን መንግሥት ከ417 እስከ 1445 ዓም የቆየ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ነበረ።
ተቋሙ በ417 ዓም በቢዛንታይን ንጉሥ 2 ቴዎዶስዮስ ተመሠረተ። ከ31 መንበሮቹ 16 ግሪክኛ፣ 15 ሮማይስጥ ሲሆኑ ያስተማሯቸው ዘርፎች ሕግ፣ ፍልስፍና፣ ሕክምና፣ ሥነ ቁጥር፣ ጂዎሜትሪ፣ ሥነ ፈለክ፣ ሙዚቃ፣ ንግግርን ማሣመር እና ሌሎች ነበሩ። እስከ 1196 ዓም (ፈረንጅ መስቀለኞች ከተማውን የያዙበት ወቅት) ድረስ፣ የክርስትናዊ መንግሥት ተቋም ነበር፤ ፍልስፍናቸውም የፕላቶና የአሪስጣጣሊስ ልማዶች ቀጠሉ። ከ1196 ዓም በኋላ እንደ ቤተ ክርስቲያን ተቋም እስከ 1445 ዓም ድረስ ቆየ፣ በዚያም ወቅት ኦቶማን ቱርኮች ከተማውን ያዙ። ጥንታዊው ትምህርት ማዕከል ለአውሮፓ በቱርኮች እጅ ስለ ተጨረሰ የሥነ ጥበብ ማዕከል ወደ ጣልያን ይዛወር ነበርና ለምዕራብ አውሮፓ ዘመነ ህዳሴው ተከተለ። የቱርኮችም አሸናፊ 2 መህመት የእስልምና ትምህርት ቤት በሥፍራው አቆመ፣ ይህም ዛሬ የኢስታንቡል ዩኒቬርሲቲ ሆኖአል።