ሥነ ቁጥር
ሥነ ቁጥር ወይንም በእንግሊዝኛ "አርቲሜቲክስ" ከሁሉ የሒሳብ ዘርፎች አንጋፋውና በሁሉም ሰው ጥቅም ላይ የሚውል ክፍል ነው። ሥነ ቁጥር የቁጥሮችን ቅልቅል ውጤት የሚያጠና ሲሆን ብዙ ጊዜ ቁጥሮች ሲደመሩ፣ ሲቀነሱ፣ ሲባዙና ሲካፈሉ የሚያሳዩትን ባህርይ ይመረምራል። ሒሳብ ተማሪዎች የቁጥር ኅልዮት ውጤቶችን ከፍተኛ ሥነ ቁጥር በማለት ከለተ ተለት መደመርና መቀነስ ጥናቶች ይለዩዋቸዋል።
ታሪክ
ለማስተካከልየሰው ልጆች ከጥንት ጀምሮ ሥነ ቁጥርን ተጠቅመዋል። ለምሳሌ አፍሪቃ ውስጥ የተገኘ 22፣000 ዓመት እንዳለው የሚቆጠር የአጥንቶች ቁርጥራጭ ለመቁጠርና ለመደመር ያገለግል እንደነበር ይጠቀሳል። በኋላም የግብጽ እና ባቢሎን ሰወች ቁጥርን መጻፍ እንደጀመሩና ይህን ፈጠራቸውን ለመደመርና ለመቀነስ እንደተገለገሉበት አሁን የተገኙ ቅርሶች ያስገነዝባሉ። የግብጽን የአጻጻፍ ስልት የተከተሉ ግሪኮችም በዩክሊድ እና ሌሎች የግሪክ ተማሪዎች አማካይነት ጥናቱን ለማሳደግ ችለዋል። ሆኖም እስከዚህ ዘመን የነበረው የቁጥር አጻጻፍ ስልት አቀማመጣዊ አልነበረም። ስለሆነም ለመደመርና ለመቀነስ፣ በተለይ ደግሞ ለማባዛትና ለማካፈል እጅግ የተወሳሰበና አሰልቺ ነበር።
የሒሳብና የሥነ ቁጥር እድገት ከፍተኛ እመርታ ያሳየው ሕንዳውያን ተማሪዎች ዜሮና አቀማመጣዊ አጻጻፍ ስልትን በ4ኛው ክፍለዘመን ሲፈለስፉ ነበር። ይህም አሁን በመላው አለም የሚሰራበት ህንዲ-አረብ ቁጥር (ማለቱ፡ 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 ) እንዲፈጠር አደረገ። ፊቦናቺ የተሰኘው የጣሊያን ነጋዴ የዚህን ድንቅ ቁጥር ቀመርና ጥቅም በመጽሐፉ በ1202 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ) በመጻፍና በአውሮጳ አገራት ሁሉ በማሰራጨት ታዋቂነቱ እንዲገን ሆነ።
የህንዲ-አረብ ቁጥር ስርዓት በጣም ቀላል ከመሆኑ የተነሳ የሒሳብ ትምህርት በአውሮጳ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አደረገ። ይሄው አዲሱ ስልት ለሒሳብ ጥናት መሰረት በመሆን የጥንቶቹን ሒሳብ ተማሪዎች ድንቅ ውጤቶች ከአዲሱ ስርዓት ጋር ሲነጻጻሩ እምብዛም ሆነው እንዲታዩ አደረጉ። የሂንዲ አረብ ቁጥር ስርዓት ለዘመናዊው የሒሳብ ትምህርት መነሳት ምክንያት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።
አስርዮሽ የቁጥር ስርዓት
ለማስተካከልአስርዮሽ የቁጥር ስርዓት አስር የተለያዩ ምልክቶችን በመጠቀም ቁጥሮችን የሚወከያ ስልት ነው። ከዚህ በተረፈ በአስርዮሽ ስርዓት አቀማመጣዊ ዋጋ ለያንዳንዱ ቁጥር ይሰጠዋል። በዚሁ ስርዓት ነጥብን በመጠቀም ክፍልፋዮች ከሙሉ ቁጥሮች ይለያሉ። ለምሳሌ 507.36 ፡ 5 መቶዎች፣ 0 አስሮች፣ 7 አንዶች ሲደመር 3 አስረኛወች፣ 6 መቶኛወች ን ለመወከል ይረዳል
የሥነ ቁጥር ስሌቶች
ለማስተካከልመሰረታዊው የሥነ ቁጥር ስሌቶች መደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛት እና ማካፈል ናቸው። ሌሎች ስሌቶችም በዚሁ ጥናት ስር ይካሄዳሉ። ለምሳሌ ፐርሰንቴጅ፣ ስኩየር ሩት፣ ማንሳት፣ ሎጋሪዝም ይገኛሉ።
መደመር (+)
ለማስተካከልመደመር ሁለት ተደማሪ ቁጥሮችን በማዋሃድ አንድ ድምር ውጤትን ያገኛል። ከሁለት በላይ ቁጥሮችን መደመር ሁለት ሁለት ቁጥሮችን እየደጋገሙ ከመደመር ጋር አንድ ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |