ፐራቶስ (ግሪክ፦ Πέρατος) ወይም ኤራቱስሲክዮን ነገሥታት ዝርዝር የአፒያ (በኋላ ሲክዮን) ንጉሥ ነበር። ካስቶርን የጠቀሱት ጸሐፊዎች «ኤራቱስ» 46 ዓመት እንደ ነገሠ ይላሉ።[1][2] ይህ ምናልባት 1987-1941 ዓክልበ. ግድም ያህል ነው። ኤራቱስ ከመሣፖስ ቀጥሎ እንደ ገዛ ሲሉ ፓውሳኒዩስ ግን መሣፖስን አይጠቅስም፤ ሌውኪፖስ ወንድ ልጅ ስላልነበረው የሴት ልጁ ካልቂኒያ እና የፖሠይዶን ልጅ ፐራቶስ ተከተለው ይላል።[3]

ቀዳሚው
መሣፖስ
አፒያ ንጉሥ
1987-1941 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ፕሌምናዮስ
  1. ^ የአውሳብዮስ ዜና መዋዕል
  2. ^ የጀሮም ዜና መዋዕል
  3. ^ "Classical E-Text: PAUSANIAS, DESCRIPTION OF GREECE 2.1 - 14". theoi.com (2011). በ5 February 2014 የተወሰደ.