ፕሌምናዮስ (ግሪክ፦ Πλημναῖος) በሲክዮን ነገሥታት ዝርዝር የአፒያ (በኋላ ሲክዮን) ንጉሥ ነበር። ካስቶርን የጠቀሱት ጸሐፊዎች ፕሌምናዮስ 48 ዓመት እንደ ነገሠ ይላሉ።[1][2] ይህ ምናልባት 1941-1893 ዓክልበ. ግድም ያህል ነው። ከአባቱ ፐራቱስ በኋላ እና ከልጁ ኦርጦፖሊስ በፊት ገዛ። ጸሐፊው ፓውሳኒዩስ በተረከው ትውፊት፣ የፕሌምናዮስ ሕጻን ልጆች ሁሉ እንዳለቀሱ ወዲያው ሞቱ። በመጨረሻ ግን ዴሜተር (አረመኔ ሴት ጣኦት) ማረችው፣ ልጁን ኦርጦፖሊስ አሳደገችና በሕይወት ኖረ።[3]

ቀዳሚው
ፐራቶስ
አፒያ ንጉሥ
1941-1893 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኦርጦፖሊስ
  1. ^ የአውሳብዮስ ዜና መዋዕል
  2. ^ የጀሮም ዜና መዋዕል
  3. ^ "Classical E-Text: PAUSANIAS, DESCRIPTION OF GREECE 2.1 - 14". theoi.com (2011). በ5 February 2014 የተወሰደ.