ሌውኪፖስ (ግሪክ፦ Λεύκιππος) በሲክዮን ነገሥታት ዝርዝር የአይጊያሌያ (በኋላ ሲክዮን) ንጉሥ ነበር። ካስቶርን የጠቀሱት ጸሐፊዎች (ጀሮምአውሳብዮስ) 53 ዓመት እንደ ነገሠ ይላሉ። ይህ ምናልባት 2112-2059 ዓክልበ. ግድም ያህል ነው። በዝርዝሩ ላይ ሌውኪፖስ ከጡሪማቆስ ቀጥሎና ከመሣፖስ በፊት ይገኛል። ፓውሳኒዩስ ሌውኪፖስ የጡሪማቆስ ልጅ ሲለው «መሣፖስ» ግን አይጠቅስም፤ ሌውኪፖስ ወንድ ልጅ ባይኖረውም ሴት ልጁ ካልቂንያ በፖሠይዶን አንድ ወንድ ልጅ ፐራቶስ ነበራትና ይህ ፔራቶስ ወራሽ ሆኖ ቀጥታ ከሌውኪፖስ ቀጥሎ ተከተለው። ሌሎቹ ጸሐፍት ፔራቶስ (ወይም ኤራቱስ) ከመሣፖስ ቀጥሎ እንደ ነገሠ ያደርጉታል።

ከሌውኪፖስ በኋላ ማን እንደ ቀጠለው እንግዲህ መደናገር አለ። በተጨማሪ በአርጎስ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ አፒስ በዚህ ጊዜ በፔሎፖኔሶስ ሁሉ ገዝቶ አገሩ ስለ ስሙ «አፒያ» ይባል ነበር። እንደ ተቀበለው በሲክዮን ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ስለዚሁ አፒስ ዘመን እንደዚህ ሲል ከቴልቂንና ከጤልክሲዮን ዘመናት መካከል እንደ ሆነ ይለናል። የአፒስ ዘመን ከሌውኪፖስ ቀጥሎ ሲዛወር ግን ከአርጎስ ዝርዝር መረጃ ልክ ይስማማል። በሌላ ልማድ ፖሠይዶን ከአፒስ ልጆች መካከል ተገኘ፤ አፒስም የሌውኪፖስ ተከታይ እንደ ታሠበ ይመስላል።

ቀዳሚው
ጡሪማቆስ
የአይጊያሌያ (ሲክዮን) ንጉሥ
2112-2059 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አፒስ