ፎድብገን (ወይም ኦድብገን) በአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከፊር ቦልግ የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። ፎድብገን የሴንጋን ማክ ዴላ ልጅ ነበር።

ጌናን ማክ ዴላ ልጅ ሪናል አይርላንድን ለ፮ ዓመታት ገዝቶ በሴንጋን ልጅ ፎድብገን ዕጅ ወድቆ ተገልብጦ ፎድብገን የዛኔ ከፍተኛ ንጉሥነቱን ያዘበት። ፎድብገን ፬ አመት ከገዛ በኋላ ግን በፈንታው በሪናል ልጅ ኤይርክ ልጅ በዮካይድ ማክ ኤይርክ እጅ በማግ ምዊርጠምኔ ወድቆ ተገለበጠ።

ሌቦር ገባላ ኤረን («የአይርላንድ ወረራዎች መጽሐፍ»፣ 1100 ዓ.ም. ግድም) እንዳለ ከፎድብገን ዘመን አስቀድሞ በአይርላንድ ዛፎች ከቶ ቋር አልነበረባቸውም።

ቀዳሚው
ሪናል
አይርላንድ (ኤልጋ) ከፍተኛ ንጉሥ
1515-1511 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ዮካይድ ማክ ኤይርክ