ሪናል (ወይም ሪንዳይልርዮናል) በአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከፊር ቦልግ የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። ሪናል የጌናን ማክ ዴላ ልጅ ነበር።

የስታርን ልጅ ፍያካ ኬንፊናን አይርላንድን ለ፭ ዓመታት ገዝቶ በጌናን ልጅ ሪናል ዕጅ ወድቆ ተገልብጦ ሪናል የዛኔ ከፍተኛ ንጉሥነቱን ያዘበት። አብዛኛው ምንጮች ሪናል ለ፮ አመት ገዛ ሲሉ፣ ከሁሉ ቀድሞ የተቀነባበረው የላውድ አቆጣጠሮች ግን ፭ አመት ይሰጠዋል። ሪናል ከገዛ በኋላ በፈንታው በሴንጋን ማክ ዴላ ልጅ በፎድብገን እጅ ወድቆ ተገለበጠ።

ሌቦር ገባላ ኤረን («የአይርላንድ ወረራዎች መጽሐፍ»፣ 1100 ዓ.ም. ግድም) እንዳለ ከሪናል ዘመን አስቀድሞ በአይርላንድ የጦሮች ጫፎች ነጥብ አልነበራቸውም፤ እንጨት ብቻ (በትሮች) ነበሩ።

ቀዳሚው
ፍያካ ኬንፊናን
አይርላንድ (ኤልጋ) ከፍተኛ ንጉሥ
1520-1515 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ፎድብገን