ፎርባስ
ፎርባስ (Φόρβας) በግሪክ አፈ ታሪክ የአርጎስ ከተማ-አገር ንጉሥ ነበር።
ካስቶር ዘሩድን የሚጠቅሱት ጸሃፊዎች ጄሮምና አውሳብዮስ እንደሚሉ፣ ፎርባስ የአርጎስ ንጉሥ ሆኖ በአገሩ ለ35 ዓመታት ነገሠ፣ የክሪያሶስ ተከታይና ልጅ ይባላል። ፓውሳኒዮስ ግን የአርጉስ ልጅ ያደርገዋል። ቢብሊዮጤኬ ከክሪያሶስና ከገላኖር መካከል ማንምን አይጠቅስም።
በቅዱስ ጀሮም ዜና መዋዕል ለክሪያሶስ ዘመን ከሰጡት ነጥቦች መካከል፦
- በፎርባስ ፲ኛው ዓመት፣ አይሞን የተሳልያ መጀመርያ ንጉሥ ሆነ።
- በ፲፪ኛው ዓመት፣ ፎርባስ ሩድን ደሴት ያዘ።
- በ፲፱ኛው ዓመት፣ ትሮቂሎስ መጀመርያውን ባለ-አራት ፈረስ ሠረገላ (ኳድሪጋ) አዘጋጀ።
- በ፳፬ኛው ዓመት ኪውዶን የክሬታ ንጉሥ ሆነ።
- በ፴፪ኛው ዓመት ኬክሮፕስ ዲፉወስ የአክታ (በኋላ አቲካ) ንጉሥ ሆነ።
ቅዱስ አውግስጢኖስ እንደሚለን፣ ፎርባስና እናቱ መላንቶሚኬ ከመሞታቸው በኋላ በአርጎሳውያን ዘንድ እንደ አማልክት ይቆጠሩ ነበር። ደግሞ የፎርባስ ተከታይ የትሪዮፓስ ልጅ ያሱስ ያደርገዋል።
በዲዮዶሮስ ሲኩሉስ ታሪክ፣ ፎርባስ «የላፒጤስ ልጅ» ወደ ሩድ ሂዶ እባቦቹን ሁሉ ከደሴቲቱ አጠፋቸው።
ቀዳሚው ክሪያሶስ |
የአርገያ (አርጎስ) ንጉሥ | ተከታይ ትሪዮፓስ |