ክሪያሶስ (Κρίασος) በግሪክ አፈ ታሪክ የአርጎስ ከተማ-አገር ንጉሥ ነበር።

ካስቶር ዘሩድን የሚጠቅሱት ጸሃፊዎች ጄሮምአውሳብዮስ እንደሚሉ፣ ክሪያሶስ የአርጎስ ንጉሥ ሆኖ በአገሩ ለ54 ዓመታት ነገሠ፣ የአባቱ አርጉስ ተከታይ ይባላል፤ እናቱም ኤዋድኔ ተባለች። ቢብሊዮጤኬ ግን ከክሪያሱስ በፊት የአርጉስንም በኲር ኤክባሶስን ይጠቅሳል። ፓውሳኒዮስ ከአርጉስና ከፎርባስ መካከል ማንምን አይጠቅስም።

በቅዱስ ጀሮም ዜና መዋዕል ለክሪያሶስ ዘመን ከሰጡት ነጥቦች መካከል፦

  • የፒራንቶስ ልጅ ካሊጢያስ የአርጎስ ዋና ቄስ ሆነ።
  • በእርሱና በግብጽ ፈርዖን «አመኖፊስ» ዘመን፣ «ኢትዮጵያውያን ከሕንዱስ ወንዝ መጥተው በግብጽ አጠገብ ሠፈሩ» ይለናል።
  • በመጨረሻው ዓመት ኤፒዳውሮስ ከተማ ተመሠረተ።

ቅዱስ አውግስጢኖስ እንደሚለን፣ ሚስቱ መላንቶሚኬ እና ልጃቸው ፎርባስ ከመሞታቸው በኋላ በአርጎሳውያን ዘንድ እንደ አማልክት ይቆጠሩ ነበር።

ቀዳሚው
ኤክባሶስ
የአርገያ (አርጎስ) ንጉሥ
1915-1861 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ፎርባስ