ፍያካ ማክ ደልበህ
(ከፍያካ ማክ ዴልባኤጥ የተዛወረ)
ፍያካ ማክ ደልበህ በአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከቱዋጣ ዴ ዳናን ወገን የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። አባቱን ደልበህ ለዙፋኑ ተከተለው። ፍያካ ለ፲ ዓመታት እንደ ነገሠ ይዘገባል።
በሌቦር ገባላ ኤረን አባቱ ደልበህና የፍያካ ልጅ ኦሎም በካይኸር፣ የናማ ልጅ፣ የነኽታን ወንድም ተገደሉ። በኋላ የተጻፉት የአራት መምህሮች ዜና መዋዕልና የአይርላንድ ታሪክ እንደሚሉት ግን፣ ደልበህ በገዛው ልጁና ተከታዩ በፍያካ ዕጅ ተገደለ። የፍያካ እናት ኤማስ ስትሆን ሶስት ሴት ልጆች ባንባ፣ ፎድላና ኤሪው ለፍያካ ወለደችለት፤ እነዚህም የአይርላንድ ደሴት ስያሜዎች ሆኑ።
ፍያካ በራሱ በኩል ፲ አመታት ገዝቶ እርሱና የኦላም ልጅ አይ ማክ ኦላማን በዮጋን ዘእምበር እጅ ተገደሉ። ከዚያ በኋላ የዳግዳ ልጅ ከርማይት ሦስት ልጆች ማክ ኲል፣ ማክ ኬክት እና ማክ ግሬን አብረው ለንጉሥነቱ ተከተሉ።
ቀዳሚው ደልበህ |
የአይርላንድ (ባንባ) ከፍተኛ ንጉሥ 1344-1334 ዓክልበ. (አፈታሪክ) |
ተከታይ ማክ ኲል፣ ማክ ኬክት እና ማክ ግሬን |