ፋይቶፕላንክተን

ፋይቶፕላንክተኖች (/ f aɪt oʊ ˈplæ ŋktən / ) ምግብ ሰሪ ከሆኑ የፕላንክተን ዘውጎች የሚመደቡ ናቸው፤ እንዲሁም የውቅያኖስ እና የጨው አልባ ውሃማ አካላት ሥርዓተ-ምህዳሮች ቁልፍ አካል ናቸው። ስሙ የመጣው φυτόν ከሚለው የግሪክ ቃል ነው። ( phyton)፣ ትርጉሙ ' ተክል '፣ እና πλαγκτός ( planktos)፣ ትርጉሙ 'መንከራተት' ወይም 'ተንሸራታች' ማለት ነው። [1] [2]

ፋይቶፕላንክተኖች ጉልበታቸውን የሚያገኙት ዛፎች እና ሌሎች ተክሎች በመሬት ላይ እንደሚያደርጉት በብርሃን አስተፃምሮ አማካኝነት ነው። ይህ ማለት፣ ፋይቶፕላንክተኖች ከፀሀይ ብርሀን ሊያገኙ ይገባል፤ ስለዚህ በደንብ ብርሃን በሚገኝባቸው የውቅያኖሶች እና ሀይቆች ንጣፍ ( euphotic zone ) ውስጥ ይኖራሉ። ከመሬት ላይ ከሚበቅሉ ተክሎች ጋር ሲነጻጸሩ፣ ፋይቶፕላንክተኖች በሰፊ ወለል ላይ ተሰራጭተው ይገኛሉ፣ በአንፃራዊነት ለአነስተኛ ወቅታዊ መለዋወጥ የተጋለጡ እና ከዛፎች ይልቅ በጣም ፈጣን የሆነ (ቀናት እና አሥርተ ዓመታት) የምርት መጠን አላቸው። በውጤቱም፣ ፋይቶፕላንክተኖች ለአየር ንብረት መለዋወጥ በአለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት ምላሽ ይሰጣሉ።

ፋይቶፕላንክተኖች የባህር እና የጨው አልባ ውሃማ አካላት ምግብ ድር መሰረት ናቸው እናም በአለምአቀፍ የካርበን ዑደት ውስጥ ቁልፍ ተዋናዮች ናቸው። ከዓለም አቀፉ የብርሃን አስተፃምሮ እንቅስቃሴ ግማሽ ያህሉ እና ቢያንስ ግማሹን የኦክስጂን ምርትን ይሸፍናሉ ፣ ምንም እንኳን ከዓለም አቀፉ የእፅዋት ባዮማስ 1% ብቻ ቢሆኑም።

ፋይቶፕላንክተኖች ብርሃናዊ አስተፃምሮ የሚያካሂዱ ባክቴሪያዎችን ( ሰማያዊ አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች ) እና የተለያዩ አንድ ህዋሴ ፕሮቲስታ ቡድኖችን (በተለይም ባልጩት ዋቅላሚዎችን) ያካተቱ በጣም የተለያዩ ናቸው።

አብዛኛዎቹ ፋይቶፕላንክተኖች በጣም ትንሽ ከመሆናቸው የተነሳ በአጉሊ መሳሪያ ባልታገዘ ዓይን በተናጠል አይታዩም። ነገር ግን፣ በበቂ መጠን በሚገኙበት ጊዜ፣ አንዳንድ ዝርያዎች በህዋሶቻቸው ውስጥ አረጓዴ ሀመልማል እና ተጨማሪ ቀለሞች (እንደ ፋይኮቢሊፕሮቲኖች ወይም ዛንቶፊል ያሉ) በመኖራቸው ምክንያት በውሃው ወለል ላይ እንደ ቀለም ንጣፍ ሊታዩ ይችላሉ።

ፋይቶፕላንክተኖች ብርሃናዊ አስተፃምሮ የሚያካሂዱ ደቂቅ ፕሮቲስታዎች እና የፀሀይ ብርሃን በሚያርፍበት የላይኛው የባህር እና የጨው አልባ ውሃማ አካላት ወለል የሚኖሩ ባክቴሪያዎች ናቸው። በመሬት ላይ ካሉ እፅዋት በትይዩ፣ ፋይቶፕላንክተኖች በውሃ ውስጥ ዋና ምርትን ያካሂዳሉ፣ [1] በውሃ ውስጥ ከሚሟሟ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ኦርጋኒክ ውህዶችን ይፈጥራሉ። ፋይቶፕላንክተኖች እና ቀጣይ - የውሃ ውስጥ ምግብ ድር፣ [3] እና በምድር የካርቦን ዑደት ውስጥ ወሳኝ ተዋናዮች ናቸው።

ፋይቶፕላንክተኖች በጣም የተለያዩ ሲሆኑ፣ ብርሃናዊ አስተፃምሮ የሚያካሂዱ ባክቴሪያዎችን ( ሳይያኖባክቴሪያ ) እና የተለያዩ አንድህዋሴ የፕሮቲስታ ቡድኖችን (በተለይም ባልጩት ዋቅላሚዎችን) ያካተቱ ናቸው። ኮኮሊቶፎረስ እና ዳይኖፍላጅላታዎችን ጨምሮ እንደ ፋይቶፕላንክተን የተሰየሙ ሌሎች ብዙ አካላት አሁን አይካተቱም ምክንያቱምብርሃናዊ አስተፃምሮ የሚያካሂዱ ብቻ ሳይሆን መብላትም ይችላሉ። [4] እነዚህ ፍጥረታት አሁን ይበልጥ በትክክል ሚክኮፕላንክተን ተብለው ተጠርተዋል። [5] ይህ እውቅና የፕላንክቶኒክ ምግብ ድርን ተግባር እንዴት እንደምንመለከት ጠቃሚ ውጤቶች አሉት። [6]

ባልጩት ዋቅላሚዎች በጣም የተለመዱ ከሆኑ የፋይቶፕላንክተን አይነቶች ውስጥ ናቸው።
የሲያኖባክቴሪያ ዝርያ (ሲሊንድሮስፔርመም ወገን)




ሥነ ምህዳር

ለማስተካከል
አለምአቀፍ የውቅያኖስ ፋይቶፕላንክተኖች ስርጭት-ናሳ

ፋይቶፕላንክተን ሃይልን የሚያገኘው ብርሃናዊ አስተፃምሮ ሂደት ነውስለዚህም በደንብ የፀሀይ ብርሃን በሚያገኘው የውቅያኖስየባህርየሐይቅ ወይም የሌላ የውሃ አካል ወለል ንጣፍ ውስጥ መኖር አለበት። በምድር ላይ ካሉት የብርሃናዊ አስተፃምሮ እንቅስቃሴዎች ግማሽ ያህሉን ፋይቶፕላንክተን ይይዛል። በካርቦን ውህዶች ውስጥ ያለው የኃይል ጥርቅም ( ዋና ምርት ) ለአብዛኛዎቹ የውቅያኖስ እንዲሁም ለብዙ የጨው አልባ ውሃማ አካላት ምግብ ድር መሠረት ነው ( ኬሞሲንተሲስ በልዩነት ወጣ ያለ ነው)።

ከሞላ ጎደል ሁሉም የፋይቶፕላንክተን ዝርያዎች የግዴታ ብርሃናዊ አስተፃምሮ የሚያካሂዱ ናቸው፣ ጥቂቶቹ ድብልቅ እና ሌሎች፣ ሀመልማል አልባ ዝርያዎች በትክክል ኢምግብ ሰሪ ናቸው (የኋለኞቹ ብዙውን ጊዜ እንደ ዙፕላንክተን ይታያሉ). [1] [7] ከእነዚህ ውስጥ በጣም የታወቁት እንደ ኖክቲሉካ እና ዳይኖፋይሲስ ያሉ ዲኖፍላጀሌት ወገኖች ናቸው፣ እነዚህም ሌሎች ህዋሳትን ወይም ብስባሽ ነገሮችን ወደ ውስጥ በማስገባት ኦርጋኒክ ካርቦን ያገኛሉ።

ፋይቶፕላንክተን ብርሃናዊ አስተፃምሮ የሚያካሂዱብርሃናዊ አስተፃምሮ በሚቻልበት የውቅያኖስ ክፍል ወይም ፎቲክ ዞን ውስጥ ይኖራል። በብርሃናዊ አስተፃምሮ ጊዜ ካርቦን ዳይኦክሳይድን ያዋህዱ እና ኦክስጅንን ያስወጣሉ። የፀሐይ ጨረር በጣም ከፍተኛ ከሆነ፣ ፋይቶፕላንክተን የፎቶ ዲግራዴሽን ሰለባ ሊሆን ይችላል። የፋይቶፕላንክተን ዝርያዎች ብዙ አይነት የብርሃናዊ አስተፃምሮ ቀለም ያላቸው ሲሆን የተለያዩ ዝርያዎች በውሃ ውስጥ በተለያዩ የሞገድ ርዝመቶች የሚገኙ የብርሃን ጨረሮችን እንዲወስዱ ያስችላቸዋል። [8] ይህ የሚያመለክተው የተለያዩ ዝርያዎች የብርሃንን የሞገድ ርዝመት በብቃት ሊጠቀሙ ይችላሉ እና ብርሃኑ አንድ ነጠላ ሥነ-ምህዳራዊ ሀብት ሳይሆን እንደ ስፔክራል ስብጥሩ ብዙ ሀብት ነው። [9] በዚያም በብርሃን ስፔክትረም ላይ የሚደረጉ ለውጦች ብቻ ተመሳሳይ ጥንካሬ ቢኖርም ተፈጥሯዊ የፋይቶፕላንክተን ዘውጎችን ሊቀይሩ እንደሚችሉ ተረጋግጧል። [10] ለእድገት ፣ የፋይቶፕላንክተን ህዋሳት በተጨማሪ ወደ ውቅያኖስ ውስጥ በወንዞች ፣ከአህጉራት መሸርሸር እና በዋልታዎች ላይ ከሚገኙ በረዶዎች ላይ ከሚቀልጥ ውሃ በሚገቡ ንጥረ ነገሮች ላይ ይወሰናሉ። ፋይቶፕላንክተን የሟሟ ኦርጋኒክ ካርቦን (DOC) ወደ ውቅያኖስ ውስጥ ይለቃል። ፋይቶፕላንክተኖች የባህር ምግብ ድር መሰረት ስለሆነ ለ ዙፕላንክተን፣ የዓሳ እጮች እና ሌሎች ኢ-ምግብ ሰሪ ፍጥረታት እንደ ታዳኝ ሆነው ያገለግላሉ። በተጨማሪም በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ ሊሲስ ሊበሰብሱ ይችላሉ። ምንም እንኳን አንዳንድ እንደ ዳይኖፍላጅላታ ያሉ የፋይቶፕላንክተን ህዋሶች አቀበታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ቢችሉም፣ ከሞገድ በተቃራኒ የሆነ እንስቃሴ በንቃት ማድረግ ግን አይችሉም። ስለዚህ ቀስ በቀስ ሰምጠው በመጨረሻ የባህር ወለልን በሟች ህዋሳት እና በብስባሽ ያዳብራሉ።

የባህር ፋይቶፕላንክተኖች ኡደት[11]

ፋይቶፕላንክተን ወሳኝ በሆኑ ንጥረ ነገሮች ላይ ጥገኛ ነው። እነዚህ በዋነኝነት በብዛት የሚያስፈልጉ ሲሆኑ እንደ ናይትሬት ፣ ፎስፌት ወይም ሲሊሲክ አሲድ ያሉት ናቸው ፣ እነዚህም በአንጻራዊነት በዛ ባለ መጠን ለእድገት የሚፈለጉ ናቸው። በውቅያኖስ ላይ ተደራሽነታቸው የሚወሰነው ባዮሎጂካል ፓምፕ ተብሎ በሚጠራው እና ጥልቀት ባለው በንጥረ-ምግብ የበለፀገ ውሃ መካከል ባለው ሚዛን ነው። የፋይቶፕላንክተን ስቶይቺዮሜትሪክ ንጥረ ነገር ስብጥር የሚመራው በውቅያኖሶች ሰፊው የላይኛው ንጣፍ ላይ በሚገኙት አጠቃላይ የማክሮ ንጥረ ነገሮች የሬድፊልድ ጥምርታ ነው። የፋይቶፕላንክተኖች እድገት እና ዘውጋዊ ስብጥር እንደ ብረት (Fe)፣ ማንጋኒዝ (Mn)፣ ዚንክ (Zn)፣ ኮባልት (Co)፣ ካድሚየም (Cd) እና መዳብ (Cu) ባሉ አስፈላጊ ማይክሮ ንጥረነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው። [12] የእነዚህ ብረቶች እጥረት ወደ ተጓዳኝ ገደቦች እና የፋይቶፕላንክተን ዘውጋዊ የመዋቅር ለውጦችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። [13] [14] እንደ ደቡብ ውቅያኖስ ባሉ ሰፊ የውቅያኖሶች ቦታዎች ላይ ፣ ፋይቶፕላንክተኖች ብዙውን ጊዜ በማይክሮ አይረን እጥረት ይገደባሉ። [15] ይህም አንዳንድ ሳይንቲስቶች በሰው አማካኝነት ወደ ከባቢ አየር ውስጥ የሚለቀቀውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ (CO 2 ) ክምችት ለመከላከል የብረት ማዳበሪያን እንዲደግፉ አድርጓቸዋል። [16] ትላልቅ ሙከራዎች የፋይቶፕላንክተን እድገትን ለማበረታታት እና የከባቢ አየርን ወደ ውቅያኖስ ውስጥ ለመሳብ ብረት (በተለምዶ እንደ ferrous ሰልፌት ያሉ ጨዎችን) ወደ ውቅያኖሶች ጨምረዋል። ስነ-ምህዳሩን የመቀየር እና የብረት ማዳበሪያው ውጤታማነት ውዝግብ እንደዚህ አይነት ሙከራዎችን አቀዝቅዟል። [17] [18] የውቅያኖስ ሳይንስ ማህበረሰብ አሁንም የብረት ማዳበሪያ ጥናትን እንደ የባህር ካርቦን ዳይኦክሳይድ ማስወገጃ (mCDR) ጥናት በመመልከት ዙረያ የተከፋፈለ አመለካከት አለው። [19] [20]

በባህር ዳርቻ ላይ በሚከሰተው ማዕበል መነቃቃት የተቀሰቀሰ በፋይቶፕላንክተን ውስጥ ያለው ባዮሊሚንሴንስ

ፋይቶፕላንክተን በሕይወት ለመትረፍ የቪታሚን-ቢ ላይ ጥገኛ ነው። በውቅያኖስ ውስጥ ያሉ አካባቢዎች የአንዳንድ ቢ ቪታሚኖች እና በተመሳሳይ የፋይቶፕላንክተን እጥረት እንዳለባቸው ተለይተዋል። [21]

በሰው ልጆች አማካኝነት የሚመጣው የሙቀት መጨመር በአለም አቀፉ የፋይቶፕላንክተን ቡድን ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ በሂደት ላይ ያለ የምርምር ርእስ ነው። በውሃው ዓምዳዊ ስትራቲፊኬሽን ላይ የተደረጉ ለውጦች፣ የሙቀት መጠን ላይ ጥገኛ የሆኑ ስነህይወታዊ አፀግብሮቶች እና ከከባቢ አየር የሚገኘው የንጥረ ነገሮች አቅርቦት ለወደፊቱ የፋይቶፕላንክተን ምርታማነት ላይ ወሳኝ ተጽእኖ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሰውልጆች ምክኒያተ የሚፈጠር የውቅያኖስ አሲዳማነት በፋይቶፕላንክተን እድገት እና ዘውጋዊ መዋቅር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖም ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል። የኮኮሊቶፎር ፋይቶፕላንክተን ህዋሶች ኮኮስፌር በሚባል የካልሲየም ካርቦኔት ሼል ውስጥ ይሸፈናሉ፣ ይህም ሽፋን ለውቅያኖስ አሲዳማነት ትብ ነው ። በአጭር የትውልድ ጊዜያቸው ምክንያት፣ አንዳንድ ፋይቶፕላንክተኖች በካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን በፍጥነት (ከወር እስከ አመት) መጨመር ምክኒያት ከሚመጣው የፒኤች መጠን ለውጥ ጋር መላመድ እንደሚችሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። [22] [23]

ፋይቶፕላንክተኖች የውሃ ውስጥ ምግብ ድር መሰረት ሆኖ ያገለግላሉ፣ ይህም ለሁሉም የውሃ ህይወት አስፈላጊ የሆነ የስነ ምህዳር ተግባር በማቅረብ ነው። ወደፊት፣ የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ወደ ሙቀት መጨመር እና ወደ ውቅያኖስ አሲዳማነት ካመራ፣ ዙፕላንክተኖች ፋይቶ ፕላንክተኖችን የሚመገቡበት ፍጥነት በመቀየሩ ምክኒያት የፋይቶፕላንከተኖች የሞት መጠን መቀየር ትኩረት የሚሻ ሊሆን ይችላል። ከውቅያኖስ የምግብ ሰንሰለቶች መካከል ባለው አጭር መስመር የሚታወቀው፣ ፋይቶፕላንከተን ክሪል(ከጥቃቅን ሽሪምፕ ጋር የሚመሳሰል ክሪስታስያን )ን ተመግቦ እርሱ ደግሞ በባሊን አሳ ነባሪዎች የሚበላበት የምግብ ሰንሰለት ነው።

በኢኳቶሪያል ፓስፊክ አካባቢ ያለው የኤልኒኖ-ደቡብ መወዛወዝ (ENSO) ዑደቶች በፋይቶፕላንክተን ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። [24] በ ENSO ዑደቶች ወቅት ባዮኬሚካላዊ እና አካላዊ ለውጦች የፋይቶፕላንክተን ዘውጋዊ መዋቅርን ይቀይራሉ። [24] እንዲሁም በፋይቶፕላንክተን አወቃቀር ላይ የሚከሰቱ ለውጦች ለምሳሌ የባዮማስ እና የፋይቶፕላንክተን ጥግግት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ በተለይም በኤልኒኖ ጊዜአት ሊከሰቱ ይችላሉ። [25] ፋይቶፕላንክተኖች ለከባቢያዊ ለውጦች ትብ ናቸው፣ ለዚህ ነው የኤስቹዋሪዎችን እና የባህር ዳርቻዎችን ስርዓተ ምህዳር ለማመልከት ጥቅም ላይ የሚውሉት። [26] እነዚህን ሁነቶች ለማጥናት በሳተላይት የታገዘ የውቅያኖስ ቀለም ምልከታ ይደረጋል፣ የሳተላይት ምስሎች አለም አቀፋዊ ስርጭታቸውን በተመለከተ ግልፅ እይታ ይሰጣሉ። [24]

ተለያይነት

ለማስተካከል

 ፋይቶፕላንክተን የሚለው ቃል በውሀ ውስጥ የምግብ መረብ የሚሳተፉትን ሁሉንም ምግብ ሰሪ ደቂቅ አካላት የሚያካትት ነው። ነገር ግን አብዛኞቹ ምግብ ሰሪዎች ተክሎች ከሆኑበት የመሬት ዘውግ በተለየ ፋይቶፕላንክተን እንደ ፕሮቲስታ፣ ውንባክቴሪያ እና አርኬባክቴሪያዎች ያሉ የተለያዩ ቡድኖች ያሉት ነው። ወደ 5,000 የሚጠጉ የታወቁ የባህር ውስጥ ፋይቶፕላንክተን ዝርያዎች አሉ። [27] ምንም እንኳን ውስን ምግብ ያለበት ሁኔታ የኒች መለያየትን የሚገድብ ቢሆንም፣ እንደዚህ ያለ ተለያይነት መፈጠሩ ግልፅ አይደለም። [28]

ብዙ የተለያዩ የዋቅላሚ አይነቶች ቢኖሩም፣ በቁጥር ረገድ ዋና ዋና የሚባሉት የፋይቶፕላንክተን ቡድኖች ባልጩት ዋቅላሚዎችሰማያዊ አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች እና ዳይኖፍላጅላታዎች ናቸው።ኮኮሊቶፎሪድ የሚባል አንድ ቡድን ከፍተኛ መጠን ያለው ዳይሜታይል ሰልፎክሳይድን (DMS) ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ ረገድ በከፊል ድርሻውን ይወስዳል.። ዳይሜታይል ሰልፎክሳይድ ኦክሲዳይድ ሆኖ ወደ ሰልፌት በመቀየር የኤሮዞል ቅንጣጢቶች ክምችት አነስተኛ በሆነበት ስፍራ ለደመና አቀዝቃዥ አስኳሎች መፈጠር ያግዛል።ይህም በ CLAW መላ ምት መሰረት በአብዛኛው ወደ ደመና ሽፋን መጨመር እና የደመና አንፀባራቂነት ያመራል። [29] [30] የተለያዩ የፋይቶፕላንክተን ዓይነቶች በተለያዩ ሥርዓተ-ምህዳሮች ውስጥ የተለያዩ የምግብ ደረጃዎችን ይደግፋሉ። እንደ ሳርጋሶ ባህር ባሉ ንጥረነገር አጠር የውቅያኖስ ክፍሎች እና ደቡብ ፓሲፊክ ጋይር፣ ፋይቶፕላንክተኖች በዋናነት ፒኮፕላንክተን እና ናኖፕላንክተን የተባሉ አነስተኛ ህዋሳት ይኖራቸዋል(ፒኮፍላጅሌት እና ናኖፍላጅሌት በመባልም ይታወቃሉ)። እነዚህ በአብዛኛው ከሲያኖባክቴሪያ(እንደ ፕሮክሎሮኮከስ እና ሳይነኮኮከስ ካሉ) እና እንደ ማይክሮሞናስ ካሉ ፒኮዩካርዮቶች የተሰሩ ናቸው። ጠንካራ የባህር ሞገድ ወይም በርከት ያለ የመሬት ንጥረነገር ኖሯቸው የተሻለ ምርታማ በሆኑ ሥርዓተ-ምህዳሮች ውስጥ ትላልቅ ዳይኖፍላጅሌቶች ዋና የፋይቶፕላንክተን አይነቶች ሲሆኑ ከአጠቃላይ ግዝፈ-ሕይወት ትልቁን ድርሻ ይሸፍናሉ።። [31]

የእድገት ስልቶች

ለማስተካከል

በሃያኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ አልፍሬድ ሲ ሬድፊልድ የፋይቶፕላንክተን ንጥረ ነገር በጥልቅ ውቅያኖስ ውስጥ ካሉ ዋና ዋና የሟሟ ንጥረ ነገሮች ጋር ተመሳሳይነት እንዳላቸው አግኝቷል። [32] ሬድፊልድ በውቅያኖስ ውስጥ ያለው የካርቦን፡ናይትሮጅን፡ፎስፈረስ ሬሾ (106፡16፡1) የሚወሰነው በፋይቶፕላንክተኖች የፍላጎት መጠን እንደሆነ አቅርቧል። ይህም ፋይቶፕላንክተኖች በሚበሰብሱ ጊዜ ናይትሮጅንንና ፎስፈረስን መልሰው ወደ ውሃ ውስጥ ስለሚለቁት ነው። ይህ የፋይቶፕላንክተንን እና የባህር ውሀን ስቶይሺዎሜትሪ ለመግለፅ የሚያገለግለ "ሬድፊልድ ጥምርታ" እየተባለ የሚጠራው ጥምርታ የባህር ስነምህዳርን፣ ባዮጄኦኬሚስትሪን እና የፋይቶፕላንክተን ዝግመተለውጥን ለመረዳት መሰረታዊ መርህ ሆኗል። [33] ይሁን እንጂ ይህ የሬድፊልድ ጥምርታ ቋሚ ባለመሆኑ ንጥረነገሮች ከውጭ ምንጮች የሚገቡበት መንገድ [34] እና የተለያዩ እንደ የናይትሮጅን ቅንበራ፣ ዲናይትሪፊኬሽን እና አናሞክስ ያሉ በውቅያኖስ ውስጥ ያሉ ማይክሮቢያል ሂደቶች አማካኝነት የተለያየ ሊሆን ይችላል።

በአንድ ህዋሴ ዋቅላሚዎች ውስጥ ያለው ተቀያያሪ የንጥረነገሮች ሚዛን በውስጣቸው ንጥረነገሮችን የማከማቸት፣ የተለያዩ ንጥረነገሮችን የሚፈልጉ ኤንዛይሞችን የመቀያየር እና ያላቸውን የኦስሞላይት ስብጥር የመቀየር ችሎታቸውን ያሳያል። [35] የህዋሱ የተለያዩ ፍሎች የየራሳቸው የንጥረነገር ጥምርታ አላቸው። [33] ለምሳሌ ህዋሱ እንደ ብርሃን እና ንጥረነገር የሉ ነገሮችን ለመሰብሰብ የሚረዱት ፕሮቲኖች እና ክሎሮፊል ከፍተኛ የናይትሮጅን መጠን እንዲሁም ዝቅተኛ የፎስፈረስ መጠን አላቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከእድገት ጋር የተያያዙ እንደ ራይቦዝማል አር ኤን ኤ ያሉ ውህዶች ከፍተኛ የሆነ የናይትሮጅን እና የፎስፈረስ ክምችት አላቸው።

በሀብቶች ድልድል ላይ በመመስረት ፋይቶፕላንክተኖች በሦስት የተለያዩ የእድገት ስልቶች ማለትም ተራፊዎች፣ የሚያብቡ[36] እና ጠቅላዮች ተብለው ይከፈላል። ተራፊ ፋይቶፕላንክተኖች ከፍተኛ የሆነ ናይትሮጅን ለ ፎስፈረስ ጥምርታ(ከ 30 በላይ) ያላቸው ሲሆን ሀብት በሌለበት ጊዜ እነኳን ለማደግ የሚያስችላቸው መሳሪያ አላቸው። የሚያብቡ ፋይቶፕላንክተኖች ዝቅተኛ የሆነ ናይትሮጅን ለ ፎስፈረስ ጥምርታ (ከ 10 በታች) አላቸው። በርካታ የእድገት መሳሪያዎች ሲኖሯቸው ከፈጣን እድገት ጋር የተላመዱ ናቸው። ጠቅላይ ፋይቶፕላንክተኖች ከሬድፊልድ N:P ጥምርታ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የናይትሮጅን ለ ፎስፈረስ ጥምርታ ሲኖራቸውበአንጻራዊነት እኩል የሆነ የሃብት መሰብሰቢያ እና የእድገት መሳሪያዎች አሏቸው።

በብዛት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ምክንያቶች

ለማስተካከል

የ NAAMES ጥናት በኦሪገን ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና በናሳ የሳይንስ ሊቃውንት በውቅያኖስ ሥርዓተ-ምህዳር ውስጥ ያለውን የፋይቶፕላንክተን ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ለመመርመር እና እንደዚህ ያሉ ተለዋዋጭ ለውጦች በከባቢ አየር አየር ፣ ደመና እና የአየር ንብረት ላይ በምን መልኩ ተጽዕኖ እንደሚያደርጉ በ 2015 እና 2019 መካከል የተደረገ የአምስት ዓመት ሳይንሳዊ ምርምር መርሃ ግብር ነበር ነው ። NAAMES ምህፃረቃል ሲሆን (የሰሜን አትላንቲክ ኤሮሶልስ እና የባህር ውስጥ ሥርዓተ-ምህዳር ጥናት) የሚለው ይወክላል። ጥናቱ ያተኮረው በሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ ንኡስ አርክቲክ አካባቢ ነው፣ እሱም በምድር ላይ ካሉት ትላልቅ ተደጋጋሚ የፋይቶፕላንክተን ግሽበቶች አንዱ ነው። በዚህ አካባቢ ያለው የረዥም ጊዜ የጥናት ታሪክ እና የተደራሽነት ቀላልነት ሰሜን አትላንቲክን "የፋይቶፕላንክተን ኤሮሶል ልቀት በመሬት የሀይል በጀት ላይ ያለው ሚና " በሚል የነበረውን የሳይንስ መላምት የበለጠ ለመፈተሽ እና ለመረዳምቹ ቦታ አድርጎታል።[37]

NAAMES  የተተለመው የተወሰኑ የዓመታዊ የፋይቶፕላንክተን ዑደት ደረጃዎች ላይ እንዲያነጣጥር ታስቦ ነበር፡- ግሽበት የሚፈጠርበትን ጊዜ እና አመታዊ የፋይቶፕላንክተን ግሸበት በድጋሚ በሚፈጠርበት ሂደት ዙሪያ የነበሩ ክርክሮችን ለመፍታት ሲባል ግዝፈ-ሕይወት ከፍተኛ፣ዝቅተኛ፣መካከለኛ ጭማሪ እና መካከለኛ ቅናሽ የሚያሳይባቸው ጊዜአት ላይ ያተኮረ ነበር። [38] በተጨማሪም የ ‹NAAMES› ፕሮጀክት የፋይቶፕላንክተን ግሽበት ዑደቶች የደመና መፈጠር እና የአየር ንብረት ላይ በምን መልኩ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ ለመረዳት፣ በመጀመሪያ ደረጃ ምርት የሚፈጠሩትን ኤሮዞሎች ብዛት፣ መጠን እና ስብጥር መርምሯል። [39]

የፋይቶፕላንክተንን ተለያይነት በተመለከተ ተወዳዳሪ መላምቶች[40]
ከቤረንፊልድ እና ቦስ፣ 2014 የተወሰደ ምስል.[41]
ክNAAMES፣ ላንግሌ የምርምር ተቋም እና ናሳ የተገኘ ምስል [42]
በሰሜናዊ የፀደይ ወቅት በሳተላይት እንደታየው የአለም የውቅያኖስ ክሎሮፊል ክምችት አማካይ ከ1998 እስከ 2004 ነበር። ክሎሮፊል የ ፋይቶፕላንክተኖች ስርጭት እና ብዛት ጠቋሚ ነው።
አለም አቀፍ ወርሃዊ የፋይቶፕላንክተን ዝርያዎ ብዛትና ምርት መልክ (A) ዓመታዊ አማካይ ወርሃዊ የዝርያዎች ብዛት እና (B) በዝርያ ስርጭት ሞዴሎች (SDMs) የሚወሰን ወርሃዊ የዝርያዎች ለውጥ፡ የላቲቲዩድ ዝንባሌዎች በ(C) የዝርያ ብዛት እና (D) ምርት። በባለቀለም መስመሮች የተቀመጡት ዋጋዎች በእያንዳንዱ የላቲቲዩድ ዲግሪ በሶስት የተለያዩ ዝርያ ስርጭት ሞዴሎች ላይ ተመስርቶ፣ ቀዩ ጥላ የሚያሳየው ±1 ስታንዳርድ ዲቪዬሽን ከ 1000 ሞንቴ ካርሎ ሲሙሌሽኖች የተለያዩ ትንበያዎችን ከተጠቀሙ ለጀነራላይዝድ አዲቲቭ ሞዴሎች (GAM)። ከቀጭኑ የአግድመት መስመር በስተ ሰሜን በ (C) እና (D) ፣ የሞዴሉ ውጤቶች የ 9 እና የ12 ወራትን በተከታታይ የሚሸፍኑ ናቸው።[43]













በምርታማነት ላይ ተፅዕኖ ያላቸው ነገሮች

ለማስተካከል
 
የፋይቶፕላንከተን ምርታማነት ላይ ተፅዕኖ ያላቸው ነገሮች

ፋይቶፕላንክተኖች የስነህይወታዊ ፓምፕ ቁልፍ አመልካቾች ናቸው ። CO2 ለወደፊት በከባቢ አየር ውስጥ የሚኖረውን ክምችት ለመተንበይ ፋይቶፕላንክተኖች ለአካባቢአዊ ሁኔታዎች መለወጥ የሚሰጠትን ምላሽ መረዳት ቅድመ ሁኔታ ነው ።

መጠነ ሙቀት ፣ ጨረር እና የንጥረ-ምግቦች ክምችት ከ CO2 ጋር በፋይቶፕላንክተን ፊዚዮሎጂ እና ስቶይሺዮሜትሪ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ዋና ዋና አካባቢአዊ ሁኔታዎች ናቸው። [44] የፋይቶፕላንክተን ስቶይሺዮሜትሪ ወይም ንጥረ ነገራዊ ስብጥር እንደ ኮፖፖድ ፣ አሳ እና ሽሪምፕ ላሉት ሁለተኛ ደረጃ አምራቾች በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም የአመጋገብ ጥራትን ስለሚወስን እና በባህር ውስጥ ባለው የምግብ ሰንሰለት በኩል የኃይል ፍሰት ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሣድር ነው። [45]

የአየር ንብረት ለውጥ የፋይቶፕላንክተን ዘውጎችን እንደገና በማዋቀር የባህር ምግብ ድር ላይ ተያያዥ ተፅእኖ ሊያስከትል ይችላል ፣ በዚህም ወደ ውቅያኖስ ውስጠኛ ክፍል የሚጓጓዘውን የካርበን መጠን ይለውጣል። [46]

ሥዕሉ የተለያዩ የአካባቢአዊ ሁኔታዎች  በጋራ እንዴት በፋይቶፕላንክተን ምርታማነት ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩ አጠቃላይ እይታ ይሰጣል። በአለምአቀፍ ለውጥ ምክንያት እነዚህ አካባቢአዊ ሁኔታዎች ሁሉ በወደፊቱ ውቅያኖስ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል።[47] የአለም ሙቀት መጨመርን በማስመሰል የሚሞከሩ ሙከራዎች የውቅያኖስ መጠነሙቀት መጨመርን ይተነብያሉ። አስደናቂ ለውጦች በውቅያኖስ ንብርብሮሽ፣ በባህር በረዶ እና የደመናሽፋን ዝውውርና ለውጦች በውቅየኖስ ወለል ላይ የጨመረ የብርሃን አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋሉ። እንዲሁም የተቀነሰ የንጥረ-ምግብ አቅርቦት ከውቅያኖስ አሲዳማነት እና ሙቀት መጨመር ጋር አብሮ ሊከሰት እንደሚችል ይተነብያል፣ ምክንያቱም ደግሞ በውሃው አምድ ንብርብሮሽ ምክኒያት የንጥረ ነገሮች ከጥልቅ ውሃ ወደ ላይ የመቀላቀል ዐዝማሚያ በመቀነሱ ነው። [48]  

የፋይቶፕላንክተኖች ሚና

ለማስተካከል
 
በተለየዩ የባህር ከባቢዎች ውስጥ የፋይቶፕላንክተኖች ሚና

በፋይቶፕላንክተኖች ተጽዕኖ ሥር ያሉ ክፍሎች የከባቢ አየርየጋዝ ስብጥርን፣ ኢንኦርጋኒክ ንጥረነገሮችን፣ የጥቂት ንጥረነገሮች ፍሰቶችን እንዲሁም በባዮሎጂካል ሂደቶች በኩል የመተላለፍ ኡደትን ያካትታል።

በብርሀን አስተፃምሮ ሂደት የተቀነበረው ካርቦን በውቅያኖስ ጠለል ላይ በተደጋጋሚሚ ጥቅም ላይ ሲውል ከዚህ ግዝፈ-ህይወት የተወሰነ ክፍሉ ደግሞ የሚሰጥም ቅንጣጢት ሆኖ ነቀጣይነተት በለውጥ ሂደት ወደሚየለፍበት ጥልቅ ውቅያኖስ ይዘዋወራል (በድጋሚ ወደ ማዕድንነት መቀየር)።

እንደ ዙፕላንከተን ያሉ ፍጥረታት እነዚህን ፋይቶፕላንክተኖች ይመገባሉ፤ እነሱም በተራቸው በሌሎች ፍጥረታት ይበላሉ። እንደዚህ እያለ ላየኞቹ አዳኞች እስካሉበት እስከ አራተኛው ደረጃ ይሄዳል።

በግምት ከጠቅላላው የካርቦን መጠን 90% የሚሆነው በምግብ ደረጃዎች ውስጥ በስርዓተ ትንፈሳ፣ በብስባሽ እና በሟሙ ኦርጋኒክ ቁሶች መልክ ይጠፋል። ይህ በፋይቶፕላንክተን እና በባክቴሪያዎች አማካኝነት የሚካሄዱትን በድጋሚ ወደ ማእድን የመቀየር ሂደት እና የንጥረምግቦች ኡደት ቅልጥፍናን በመጠበቅ ረገድ አስፈላጊ ያደርጋቸዋል። [49]

አኳካልቸር

ለማስተካከል

ፋይቶፕላንክተኖች በአኳካልቸርም ሆነ በማሪካልቸር ውስጥ ቁልፍ የምግብ አይነት ናቸው። ሁለቱም ለሚያሳድጓቸው እንስሳት ፋይቶፕላንክተንን እንደ ምግብ ምንጭ የጠቀሙታል። በማሪካልቸር ውስጥ ፋይቶፕላንክተኖቹ በተፈጥሮ የሚገኙ ሆነው የተለመደ የውሃ ስርጭት ባለበት የተከለለ ስፍራ ውስጥ ይጨመራሉ።

በአኳካልቸር ውስጥ ፋይቶፕላንክተኖቹ መጀመሪያ መገኘት ይኖርባቸዋል፤ከዚያ በቀጥታ ይጨመራሉ። ፕላንክተኖቹ ተወሰነ የውሃ አካል ሊሰበሰቡ ይችላሉ፣ አልያም እንዲያድጉ ይደረጋል፤ ሆኖም ግን የመጀመሪያው መንገድ እምብዛም ጥቅም ላይ አይውልም።

ሮቲፈሮችን ለማሳደግ ፋይቶፕላንክተን እንደ ምግብነት ያገለግላል። ሮቲፈሮች ደግሞ በተራቸው ሌሎች እንስሳትን ለመመገብ ይውላሉ። በተጨማሪም ፋይቶፕላንክተን ሉል ኦይስተሮችን እና ግዙፍ ክላሞችን ጨምሮ የተለያዩ አይነት የአኳካልቸር ዛጎል ለበስ እንስሳትን ለመመገብም ይውላል። [50]ፋይቶፕላንክተኖች የእንቁ ኦይስተር እና ግዙፍ ክላም ጨምሮ በርካታ የውሃ ውስጥ ሞለስኮችን ለመመገብ ያገለግላል።

በ2018 የተደረገ ጥናት በአለም አቀፉ ውቅያኖስ የተፈጥሮ ፋይቶፕላንክተኖችን የምግብነት ጠቀሜታ በውስጣቸው በሚገኘው የካርቦሀይድሬት፣ ፕሮቲን እና ስብ መጠን ግምት ለመስራት ከሳተላይቶች[51] የሚገኝ የውቅያኖሶች የቀለም መረጃን ተጠቅሞ ነበር፤ እናም የፋይቶፕላንክተኖች የሀይል ሰጭነት ዋጋ በውቅያኖስ ውስጥ ከቦታ ቦታ እንዲሁም በአንድ አመት ሁለት የተለያዩ ወቅቶች መካከል ግምት ውስጥ በሚገባ መልኩ ልዩነት እንዳለው አግኝቷል።[52][53]

ፋይቶፕላንክተኖችን በአርቴፊሻል ሁኔታዎች ውስጥ ማምረት እራሱን የቻለ የአኳካልቸር አይነት ነው። ፋይቶፕላንክተኖች ለተለያዩ ዓላማዎች ሊረቡ ይችላሉ፣ ለሌሎች የውሃ ውስጥ ፍጥረታት ምግብን ጨምሮ፣ በውሃ ውስጥ ለታሰሩ ኢደንደሴዎች ተጨማሪ ምግብ ሊሆኑ ይችላሉ ። የእርባታው መጠን ከአነስተኛ እርባታ (ከ1 ሊትር በታች) እስከ ብዙ ሺህ ሊትሮች የሚሆን ገበያተኮር አኳካልቸር ሊሆን ይችላል። [54] መጠኑ ምንም ይሁን ምን ውጤታማ በሆነ መልኩ ፕላንክተኖችን ለማሳደግ መቅረብ ያለባቸው ሁኔታዎች አሉ።

አብዛኛዎቹ ለማሳደግ የሚሆኑ ፕላንክተኖች ባህራይ ናቸው፤ እናም ከ1.010 እስከ 1.026 ስፔሲፊክ ግራቪቲ ያለው የባህር ውሃ እንደ ማሳደጊያ ሊያገለግል ይችላል።እርባታውን ከሥነ ሕይወታዊ ብክለት ለመከላከል ይህ ውሃ ከጀርም ነፃ መደረግ ይኖርበታል፣ ይህም በአብዛኛው አውቶክሌቭን በመጠቀም በሙቀት ወይም ለልዕለ-ሐምራዊ ጨረር በማጋለጥ ነው።

ፕላንክተኖች ተንሳፍፈው እንዲቆዩ ለማድረግ እንዲሁም ለብርሃን አስተፃምሮ የሚሆን የሟሟ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ለማቀረብ አንድ ካልቸር በተወሰነ መንገድ አየር ሊሰጠው ወይም ሊንቀሳቀስ ያስፈልጋል። ቋሚ ከሆነ የአየር አቅርቦት በተጨማሪ አባዛኞቹ ካልቸሮች በቋሚነት ሊቀላቀሉ ወይም ሊማሰሉ ያስፈልጋል። ለፋይቶፕላንክተኖች እድገት ብርሃን መሰጠት ይኖርበታል። የብርሃኑ የቀለም ድምቀት ወደ 6500 K ገደማ መሆን ሲኖርበት ፣ ከ4,000K እስከ 20,000K የቀለም ድምቀቶች ስኬታማ በሆነ መልኩ አገልግሎት ላይ ውለዋል።ከቋሚ አየር አየር በተጨማሪ፣ አብዛኛዎቹ ባህሎች በእጅ ይደባለቃሉ ወይም በየጊዜው ይነሳሉ። ለ ፋይቶፕላንክተኖች እድገት ብርሃን መሰጠት አለበት። የመብራት ቀለም ሙቀት በግምት 6,500 ኪ.ሜ መሆን አለበት፣ ነገር ግን ከ 4,000 K እስከ 20,000 ኪ እሴቶች በተሳካ ሁኔታ ጥቅም ላይ ውለዋል።በቀን ውስጥ የብርሀን ተጋላጭነት ወደ 16 ሰዓት ገደማ መሆን አለበት፤ ይህ እጅግ በጣም ውጤታማ የሆነ አርቴፊሻል የቀን ርዝመት ነው።[55]

በሰውልጆች ምክኒያት የመጡ ለውጦች

ለማስተካከል
 
መጠነ ሙቀት ሲጨምር የፋይቶፕላንክተን ዝርያዎች ብዛት መጨመርን የሚያሳይ ንድፍ

ምንም እንኳን የባህር ውስጥ ፋይቶፕላንክተን  ከአለም አቀፉ የእፅዋት ግዝፈህይወት ~1% ብቻ ቢወክልም ከዓለም አቀፉ የብርሃናዊ አስተፃምሮ CO2 ቅንበራ ግማሹን (በዓመት ~50 ፔንታ ግራም ካርቦን የተጣራ አለምአቀፋዊ ቀዳሚ ምርት ) እና ከኦክሲጅን ምርት ግማሹን ያከናውናል።[56] ከመሬት ላይ ተክሎች ጋር ሲነጻጸር፣ የባህር ውስጥ ፋይቶፕላንክተን በሰፊ ወለል ላይ ይሰራጫሉ፣ ለአነስተኛ ወቅታዊ  ተለዋዋጭነት የተጋለጡ ሲሆኑ ከዛፎች ይልቅ በጣም ፈጣን የምርት መጠን አላቸው።(ሲነጻጸር ቀናት እና አሥርተ ዓመታት ይሆናል) [56] ስለዚህ  በአለም አቀፍ ደረጃ ፋይቶፕላንክተኖች ለአየር ንብረት  ለውጥ በፍጥነት ምላሽ ይሰጣሉ።  እነዚህ ባህሪያት አንድ ሰው ፋይቶፕላንክተኖች ለካርቦን ቅንበራ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ ሲገመግም እና በአየር ንብረት መዛባት ምክኒያት ይህ ምርት በምን መልኩ  ሊለወጥ እንደሚችል ሲተነብይ አስፈላጊ ናቸው።


የአየር ንብረት ለውጥ የአየር ንብረት ለውጥ በመጀመሪያ ደረጃ ምርት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ መተንበይ በፋይቶፕላንክተኖች የግሽበት ኡደት የተወሳሰበ ነው።  ፋይቶፕላንክተኖች የግሽበት ኡደት ላይ ደግሞ  ከታች ወደ ላይ የሆነ ቁጥጥር (ለምሳሌ የወሳኝ ንጥረ ምግቦች አቅርቦት እና አቀባዊ ድብልቆሽ) እና ከላይ ወደ ታች የሆነ ቁጥጥር(ለምሳሌ ግጦሽና ቫይረሶች) ተፅዕኖ ያደርጋሉ። [57] [56] [58] [59] [60] [61] የፀሐይ ጨረር፣ የሙቀት መጠን እና የንፁህ ውሃ ግብአቶች የገጸ ውሀዎች መጨመር የውቅያኖስ ንጣፍን ያጠናክራል እና በዚህም ምክንያት ከጥልቅ ውሃ ወደ የገፀ ምድር ውሃ የሚመጡ ንጥረ ነገሮችን ማጓጓዝ ይቀንሳል ይህም የአንደኛ ደረጃ ምርታማነትን ይቀንሳል።የፀሀይ ጨረር ፣ መጠነሙቀት እና የንፁህ ውሃ ወደ መሬት ላይ የውሃ አካላት መጨመር የውቅያኖስን ንብርብሮሽ ያጠናክረዋል ከዚያ ጋር ተያይዞ ደግሞ ከጥልቅ ውሃ ወደ ውሀ ጠለል የሚደረግ የንጥረምግቦች መጓጓዝ ይቀንሳል፤ ያም የመጀመሪያ ደረጃ ምርትን ይቀንሳል። [56] [61] [62] በተቃራኒው የCO2 መጠን መጨመር የፋይቶፕላንክተኖችን የመጀመሪያ ደረጃ ምርት ይጨምረዋል፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው የንጥረምግቦች ውስንነት በሌለ ጊዜ ብቻ ነው። [63] [64] [65]

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ባለፈው ምዕተዓመት አለማቀፉ የውቅያኖስ የፋይቶፕላንክተኖች ጥግግት ቀንሷል። ነግር ግን የረጅም ጊዜ የፋይቶፕላንክተን መረጃ ውስን ከመሆኑ፣ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች መለያየተ እና ግዙፍ የሆነ አመታዊ እና የአስርት አመታት የፋይቶፕላንክተን ምርት ተለዋዋጭነት እነዚህ ድምዳሜዎች ጥያቄ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።ከዚህም በላይ ፣ ሌሎች ጥናቶች ደግሞ የውቅያኖስ ፋይቶፕላንክተን ምርት እንደጨመረ እና በተወሰኑ ስፍራዎች ወይም የተወሰኑ የፋይቶፕላንክተን ቡድኖች ውስጥ ለውጥ እንዳለ  ይጠቁማሉ።የዓለማቀፉ የባህር በረዶ መረጃ ጠቋሚ እየቀነሰ ነው፣ ይህም ወደ ከፍተኛ የብርሃን ስርፀት እና የበለጠ የመጀመሪያ ደረጃ ምርትን ያመራል፤ ቢሆንም፣ በተለዋዋጭ ድብልቅ ቅጦች እና በንጥረ-ምግብ አቅርቦት ላይ ስለሚኖረው ለውጥ እና በዋልታ ዞኖች ውስጥ የምርታማነት አዝማሚያዎች ላይ የሚጋጩ ትንበያዎች አሉ። ይሁን እንጂ የመደባለቅ ሂደት እና የንጥረ ምግቦች አቅርቦት መለወጥ በዋልታዎች አካባቢ የሚኖረው የምርታማነት አካሄድ ላይ ስለሚኖራቸው ተፅዕኖ የሚጋጩ ትንበያዎች አሉ።

በሰው ልጅ አማካኝነት የሚመጣው የአየር ንብረት ለውጥ በፋይቶፕላንክተን ተለያይነት ላይ ያለው ተፅዕኖ በሚገባ ግንዛቤ አልተገኘበትም። አንዳንድ ሞዴሎች እንደሚተነብዩት፣ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀተ እየጨመረ ከቀጠለ በ2100  በአንድ የተወሰነ ስፋት ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ የፋይቶፕላንክተን ዝርያዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል። ይህ የፕላንክተኖች ተለያይነት መጨመር ከውቅያኖስ መጠነሙቀት መጨመር ጋር የተያያዘ ነው።በዝርያ ብዛት ከሚኖር ለውጥ በተጨማሪ፣ ፋይቶፕላንክተን የሚገኝባቸው አካባቢዎች ወደ ምድር ዋልታዎች እየተጠጉ እንደሚሄዱ ይጠበቃል። ይህ ደግሞ ሥርዓተ-ምህዳርን ሊያዛባ ይችላል፣ ምክኒያቱም ፋይቶፕላንክተኖች በዙፕላንክተኖች ይበላሉ ይህም የአሳ ምርትን የሚደግፈው የምግብ ሰንሰለት ቁልፍ አካል ነው።  ይህ የፋይቶፕላንክተኖች የስፍራ ለውጥ በሰዎች እንቅስቃሴ የተለቀቀውን ካርቦን የማጠራቀም ችሎታቸውን ሊቀንሰው ይችላል። በሰው ልጆች አማካኝነት በፋይቶፕላንክተኖች ላይ የሚመጣ ለውጥ በተፈጥሯዊ ሥርዓተ-ምህዳሮች እና ኤኮኖሚአዊ ሂደቶች ላይ ተፅዕኖ አለው። [66]

በተጨማሪም ይመልከቱ

ለማስተካከል
  • የዋቅላሚ እርሻን የሚያካትት አኳካልቸር
  • የውሂብ ጎታ ዝርያዎች
  • በውሃ ውስጥ የፕላንክቶኒክ ዋቅላሚዎች ስርጭት
  • በውሃ ዓምድ ውስጥ የሚንሳፈፉ የፕላንክተን የባክቴሪያ አካል
  • በውቅያኖሶች ውስጥ ካርቦንን የመያዝ ሂደት
  • CLAW መላምት።የባህርን ባዮታ እና የአየር ሁኔታን የሚያገናኝ መላምት አሉታዊ ግብረመልሶች
  • ወሳኝ ጥልቀት
  • ጥልቅ ክሎሮፊል ከፍተኛ
  • የጨው አልባ ውሃማ አካላት ፋይቶፕላንክተኖች
  • የብረት ማዳበሪያ ሥነ-ምህዳራዊ ጽንሰ-ሀሳብ
  • ማይክሮፋይት -
  • NAAMES
  • የውቅያኖስ አሲዳማት መጨመር]] - በውቅያኖስ ውስጥ የፒኤች መጠን መቀነስ
  • የፕላንክተን ፓራዶክስ;- ለጥቂት ሀብቶች ውድድር ቢኖርም ከፍተኛ የፕላንክተን ተለያይነት ስለመታየቱ ሥነ-ምህዳራዊ ምልከታ
  • የፋይቶፕላንክተን ጥገኛ ተውሳኮች
  • (ብርሃናዊ አስተጻምሮ የሚያካዱ ፒኮፕላንክተን)- የፎቶሲንተቲክ ፕላንክተን ቡድን
  • በውሃ አካላት ውስጥ ጥቃቅን የካልሲየም ካርቦኔት ቅንጣቶችን መንሳፈፍ
  • የፕላንክተን ጉባኤዎች(ቀጭን ንብርብሮች (የውቅያኖስ ታሪክ)



ተጨማሪ ንባብ
ለማስተካከል
  • Greeson, Phillip E.. An annotated key to the identification of commonly occurring and dominant genera of Algae observed in the Phytoplankton of the United States. 
  • Kirby, Richard R.. Ocean Drifters: A Secret World Beneath the Waves. 
  • Martin, Ronald; Quigg, Antonietta. "Tiny Plants That Once Ruled the Seas". Scientific American 308 (6): 40–5. doi:10.1038/scientificamerican0613-40. Bibcode2013SciAm.308f..40M. 

ውጫዊ አገናኞች

ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል
  1. ^ Pierella Karlusich, Juan José. Phytoplankton in the Tara Ocean. 
  2. ^ Pierella Karlusich, Juan José (2020). Exploration of marine phytoplankton: from their historical appreciation to the omics era. 
  3. ^ Ghosal; Rogers; Wray, S.; M.; A.. "The Effects of Turbulence on Phytoplankton". Aerospace Technology Enterprise. NTRS.
  4. ^ Mitra, Aditee; Caron, David A.; Faure, Emile; Flynn, Kevin J.; Leles, Suzana Gonçalves; Hansen, Per J.; McManus, George B.; Not, Fabrice et al. (27 February 2023). "The Mixoplankton Database (MDB): Diversity of photo-phago-trophic plankton in form, function, and distribution across the global ocean" (in en). Journal of Eukaryotic Microbiology 70 (4): e12972. doi:10.1111/jeu.12972. ISSN 1066-5234. PMID 36847544. https://onlinelibrary.wiley.com/doi/10.1111/jeu.12972. 
  5. ^ Flynn, Kevin J; Mitra, Aditee; Anestis, Konstantinos; Anschütz, Anna A; Calbet, Albert; Ferreira, Guilherme Duarte; Gypens, Nathalie; Hansen, Per J et al. (2019-07-26). "Mixotrophic protists and a new paradigm for marine ecology: where does plankton research go now?" (in en). Journal of Plankton Research 41 (4): 375–391. doi:10.1093/plankt/fbz026. ISSN 0142-7873. https://academic.oup.com/plankt/article/41/4/375/5531601. 
  6. ^ Glibert, Patricia M.; Mitra, Aditee (2022-01-21). "From webs, loops, shunts, and pumps to microbial multitasking: Evolving concepts of marine microbial ecology, the mixoplankton paradigm, and implications for a future ocean". Limnology and Oceanography 67 (3): 585–597. doi:10.1002/lno.12018. ISSN 0024-3590. http://dx.doi.org/10.1002/lno.12018. 
  7. ^ Mitra, Aditee; Flynn, Kevin J.; Tillmann, Urban (2016-04-01). "Defining Planktonic Protist Functional Groups on Mechanisms for Energy and Nutrient Acquisition: Incorporation of Diverse Mixotrophic". Protist 167 (2): 106–120. doi:10.1016/j.protis.2016.01.003. ISSN 1434-4610. PMID 26927496. 
  8. ^ Kirk, John T. O. (1994). Light and Photosynthesis in Aquatic Ecosystems. doi:10.1017/cbo9780511623370. https://www.cambridge.org/core/books/light-and-photosynthesis-in-aquatic-ecosystems/C19B28AE07B1CDEBDA5593194DE4E304. 
  9. ^ Stomp, Maayke; Huisman, Jef; de Jongh, Floris; Veraart, Annelies J.; Gerla, Daan; Rijkeboer, Machteld; Ibelings, Bas W.; Wollenzien, Ute I. A. et al. (November 2004). "Adaptive divergence in pigment composition promotes phytoplankton biodiversity" (in en). Nature 432 (7013): 104–107. doi:10.1038/nature03044. ISSN 1476-4687. PMID 15475947. Bibcode2004Natur.432..104S. https://www.nature.com/articles/nature03044. 
  10. ^ Hintz, Nils Hendrik; Zeising, Moritz; Striebel, Maren (2021). "Changes in spectral quality of underwater light alter phytoplankton community composition" (in en). Limnology and Oceanography 66 (9): 3327–3337. doi:10.1002/lno.11882. ISSN 1939-5590. Bibcode2021LimOc..66.3327H. https://onlinelibrary.wiley.com/doi/abs/10.1002/lno.11882. 
  11. ^ Käse L, Geuer JK. (2018) "Phytoplankton responses to marine climate change–an introduction". In Jungblut S., Liebich V., Bode M. (Eds) YOUMARES 8–Oceans Across Boundaries: Learning from each other, pages 55–72, Springer. doi:10.1007/978-3-319-93284-2_5.  Material was copied from this source, which is available under a Creative Commons Attribution 4.0 International License.
  12. ^ Sunda, William (2012-06-07). "Feedback Interactions between Trace Metal Nutrients and Phytoplankton in the Ocean". Frontiers in Microbiology 3. doi:10.3389/fmicb.2012.00204. ISSN 1664-302X. PMID 22701115. 
  13. ^ Browning, Thomas J.; Moore, C. Mark (2023-08-17). "Global analysis of ocean phytoplankton nutrient limitation reveals high prevalence of co-limitation". Nature Communications 14 (1): 5014. doi:10.1038/s41467-023-40774-0. ISSN 2041-1723. PMID 37591895. Bibcode2023NatCo..14.5014B. 
  14. ^ Moore, C. M.; Mills, M. M.; Arrigo, K. R. (September 2013). "Processes and patterns of oceanic nutrient limitation". Nature Geoscience 6 (9): 701–710. doi:10.1038/ngeo1765. ISSN 1752-0908. Bibcode2013NatGe...6..701M. 
  15. ^ Tagliabue, Alessandro; Bowie, Andrew R.; Boyd, Philip W. (March 2017). "The integral role of iron in ocean biogeochemistry". Nature 543 (7643): 51–59. doi:10.1038/nature21058. ISSN 1476-4687. PMID 28252066. Bibcode2017Natur.543...51T. 
  16. ^ Richtel, M. (1 May 2007). "Recruiting Plankton to Fight Global Warming". The New York Times. 
  17. ^ Monastersky, Richard. "Iron versus the Greenhouse: Oceanographers Cautiously Explore a Global Warming Therapy". Science News 148 (14): 220–1. doi:10.2307/4018225. 
  18. ^ Buesseler, Ken O.; Bianchi, Daniele; Chai, Fei (2024-09-09). "Next steps for assessing ocean iron fertilization for marine carbon dioxide removal". Frontiers in Climate 6. doi:10.3389/fclim.2024.1430957. ISSN 2624-9553. 
  19. ^ You must specify title = and url = when using {{cite web}}."".
  20. ^ Cullen, John J.; Boyd, Philip W. (2008-07-29). "Predicting and verifying the intended and unintended consequences of large-scale ocean iron fertilization". Marine Ecology Progress Series 364: 295–301. doi:10.3354/meps07551. ISSN 0171-8630. Bibcode2008MEPS..364..295C. 
  21. ^ Sañudo-Wilhelmy, Sergio (2012-06-23). "Existence of vitamin 'deserts' in the ocean confirmed". ScienceDaily.
  22. ^ Collins, Sinéad; Rost, Björn; Rynearson, Tatiana A. (2013-11-25). "Evolutionary potential of marine phytoplankton under ocean acidification" (in en). Evolutionary Applications 7 (1): 140–155. doi:10.1111/eva.12120. ISSN 1752-4571. PMID 24454553. 
  23. ^ Lohbeck, Kai T.; Riebesell, Ulf; Reusch, Thorsten B. H. (2012-04-08). "Adaptive evolution of a key phytoplankton species to ocean acidification" (in En). Nature Geoscience 5 (5): 346–351. doi:10.1038/ngeo1441. ISSN 1752-0894. 
  24. ^ Masotti, I.; Moulin, C.; Alvain, S.; Bopp, L.; Tagliabue, A.; Antoine, D. (4 March 2011). "Large-scale shifts in phytoplankton groups in the Equatorial Pacific during ENSO cycles". Biogeosciences 8 (3): 539–550. doi:10.5194/bg-8-539-2011. Bibcode2011BGeo....8..539M. 
  25. ^ Sathicqab, María Belén; Bauerac, Delia Elena; Gómez, Nora (15 September 2015). "Influence of El Niño Southern Oscillation phenomenon on coastal phytoplankton in a mixohaline ecosystem on the southeastern of South America: Río de la Plata estuary". Marine Pollution Bulletin 98 (1–2): 26–33. doi:10.1016/j.marpolbul.2015.07.017. Bibcode2015MarPB..98...26S. 
  26. ^ Sathicq, María Belén; Bauer, Delia Elena; Gómez, Nora (15 September 2015). "Influence of El Niño Southern Oscillation phenomenon on coastal phytoplankton in a mixohaline ecosystem on the southeastern of South America: Río de la Plata estuary". Marine Pollution Bulletin 98 (1–2): 26–33. doi:10.1016/j.marpolbul.2015.07.017. Bibcode2015MarPB..98...26S. 
  27. ^ Hallegraeff, G.M.. Manual on Harmful Marine Microalgae. pp. 25–49. 
  28. ^ Hutchinson, G. E.. "The Paradox of the Plankton". The American Naturalist 95 (882): 137–45. doi:10.1086/282171. 
  29. ^ Charlson, Robert J.; Lovelock, James E.; Andreae, Meinrat O.. "Oceanic phytoplankton, atmospheric sulphur, cloud albedo and climate". Nature 326 (6114): 655–61. doi:10.1038/326655a0. Bibcode1987Natur.326..655C. 
  30. ^ Quinn, P. K.; Bates, T. S.. "The case against climate regulation via oceanic phytoplankton sulphur emissions". Nature 480 (7375): 51–6. doi:10.1038/nature10580. PMID 22129724. Bibcode2011Natur.480...51Q. 
  31. ^ Calbet, A.. "The trophic roles of microzooplankton in marine systems". ICES Journal of Marine Science 65 (3): 325–31. doi:10.1093/icesjms/fsn013. 
  32. ^ Redfield, Alfred C.. James Johnstone Memorial Volume. pp. 176–92. 
  33. ^ Arrigo, Kevin R.. "Marine microorganisms and global nutrient cycles". Nature 437 (7057): 349–55. doi:10.1038/nature04159. PMID 16163345. Bibcode2005Natur.437..349A. 
  34. ^ Fanning, Kent A.. "Influence of atmospheric pollution on nutrient limitation in the ocean". Nature 339 (6224): 460–63. doi:10.1038/339460a0. Bibcode1989Natur.339..460F. 
  35. ^ Klausmeier, Christopher A.; Litchman, Elena; Levin, Simon A.. "Phytoplankton growth and stoichiometry under multiple nutrient limitation". Limnology and Oceanography 49 (4 Part 2): 1463–70. doi:10.4319/lo.2004.49.4_part_2.1463. 
  36. ^ Klausmeier, Christopher A.; Litchman, Elena; Daufresne, Tanguy; Levin, Simon A. (2004). "Optimal nitrogen-to-phosphorus stoichiometry of phytoplankton". Nature. 429 (6988): 171–4. Bibcode:2004Natur.429..171K. doi:10.1038/nature02454. PMID 15141209. S2CID 4308845
  37. ^ Behrenfeld, Michael J.; Moore, Richard H.; Hostetler, Chris A.; Graff, Jason; Gaube, Peter; Russell, Lynn M.; Chen, Gao; Doney, Scott C.; Giovannoni, Stephen; Liu, Hongyu; Proctor, Christopher (22 March 2019). "The North Atlantic Aerosol and Marine Ecosystem Study (NAAMES): Science Motive and Mission Overview". Frontiers in Marine Science. 6: 122. doi:10.3389/fmars.2019.00122. ISSN 2296-7745
  38. ^ Behrenfeld, Michael J.; Moore, Richard H.; Hostetler, Chris A.; Graff, Jason; Gaube, Peter; Russell, Lynn M.; Chen, Gao; Doney, Scott C. et al. (2019-03-22). "The North Atlantic Aerosol and Marine Ecosystem Study (NAAMES): Science Motive and Mission Overview". Frontiers in Marine Science 6: 122. doi:10.3389/fmars.2019.00122. ISSN 2296-7745. 
  39. ^ Engel, Anja; Bange, Hermann W.; Cunliffe, Michael; Burrows, Susannah M.; Friedrichs, Gernot; Galgani, Luisa; Herrmann, Hartmut; Hertkorn, Norbert et al. (2017-05-30). "The Ocean's Vital Skin: Toward an Integrated Understanding of the Sea Surface Microlayer". Frontiers in Marine Science 4. doi:10.3389/fmars.2017.00165. ISSN 2296-7745. 
  40. ^ Cite error: Invalid <ref> tag; no text was provided for refs named Behrenfeld2018
  41. ^ Behrenfeld, Michael J.; Boss, Emmanuel S. (2014-01-03). "Resurrecting the Ecological Underpinnings of Ocean Plankton Blooms". Annual Review of Marine Science 6 (1): 167–194. doi:10.1146/annurev-marine-052913-021325. ISSN 1941-1405. PMID 24079309. Bibcode2014ARMS....6..167B. 
  42. ^ NAAMES: Science - Objectives Langley Research Center, NASA, Updated: 6 June 2020. Retrieved: 15 June 2020.
  43. ^ Righetti, D., Vogt, M., Gruber, N., Psomas, A. and Zimmermann, N.E. (2019) "Global pattern of phytoplankton diversity driven by temperature and environmental variability". Science advances, 5(5): eaau6253. doi:10.1126/sciadv.aau6253.  Material was copied from this source, which is available under a Creative Commons Attribution 4.0 International License
  44. ^ Moreno, Allison R.; Hagstrom, George I.; Primeau, Francois W.; Levin, Simon A.; Martiny, Adam C.. "Marine phytoplankton stoichiometry mediates nonlinear interactions between nutrient supply, temperature, and atmospheric CO2". Biogeosciences 15 (9): 2761–2779. doi:10.5194/bg-15-2761-2018. 
  45. ^ Li, Wei; Gao, Kunshan; Beardall, John. "Interactive Effects of Ocean Acidification and Nitrogen-Limitation on the Diatom Phaeodactylum tricornutum". PLOS ONE 7 (12): e51590. doi:10.1371/journal.pone.0051590. PMID 23236517. 
  46. ^ Irwin, Andrew J.; Finkel, Zoe V.; Müller-Karger, Frank E.; Troccoli Ghinaglia, Luis. "Phytoplankton adapt to changing ocean environments". Proceedings of the National Academy of Sciences 112 (18): 5762–5766. doi:10.1073/pnas.1414752112. PMID 25902497. 
  47. ^ Häder, Donat-P.; Villafañe, Virginia E.; Helbling, E. Walter. "Productivity of aquatic primary producers under global climate change". Photochem. Photobiol. Sci. 13 (10): 1370–1392. doi:10.1039/C3PP50418B. PMID 25191675. 
  48. ^ Sarmiento, J. L.; Slater, R.; Barber, R.; Bopp, L.; Doney, S. C.; Hirst, A. C.; Kleypas, J.; Matear, R. et al.. "Response of ocean ecosystems to climate warming". Global Biogeochemical Cycles 18 (3): n/a. doi:10.1029/2003GB002134. 
  49. ^ Lalli, Carol M. (16 May 1997). Biological oceanography an introduction. Elsevier Science. ISBN 978-0-7506-3384-0. OCLC 837077589. http://worldcat.org/oclc/837077589. 
  50. ^ Cite error: Invalid <ref> tag; no text was provided for refs named sroy
  51. ^ Roy, Shovonlal (12 February 2018). "Distributions of phytoplankton carbohydrate, protein and lipid in the world oceans from satellite ocean colour". The ISME Journal. 12 (6): 1457–1472. Bibcode:2018ISMEJ..12.1457R. doi:10.1038/s41396-018-0054-8. ISSN 1751-7370. PMC 5955997. PMID 29434313
  52. ^ Roy, Shovonlal (12 February 2018). "Distributions of phytoplankton carbohydrate, protein and lipid in the world oceans from satellite ocean colour". The ISME Journal. 12 (6): 1457–1472. Bibcode:2018ISMEJ..12.1457R. doi:10.1038/s41396-018-0054-8. ISSN 1751-7370. PMC 5955997. PMID 29434313
  53. ^ "Nutrition study reveals instability in world's most important fishing regions"
  54. ^ Cite error: Invalid <ref> tag; no text was provided for refs named mcvey
  55. ^ McVey, James P., Nai-Hsien Chao, and Cheng-Sheng Lee. CRC Handbook of Mariculture Vol. 1 : Crustacean Aquaculture. New York: CRC Press LLC, 1993.
  56. ^ Behrenfeld. Climate-mediated dance of the plankton. 
  57. ^ Hutchins. Marine phytoplankton and the changing ocean iron cycle. 
  58. ^ De Baar. Importance of iron for plankton blooms and carbon dioxide drawdown in the Southern Ocean. 
  59. ^ Boyd. Mesoscale Iron Enrichment Experiments 1993-2005: Synthesis and Future Directions. Archived from the original on 2020-11-02. https://web.archive.org/web/20201102032923/https://pure.rug.nl/ws/files/2797658/2007ScienceBoyd.pdf በ2024-11-02 የተቃኘ. 
  60. ^ Behrenfeld. Revaluating ocean warming impacts on global phytoplankton. 
  61. ^ Behrenfeld. Annual boom–bust cycles of polar phytoplankton biomass revealed by space-based lidar. 
  62. ^ Behrenfeld. Climate-driven trends in contemporary ocean productivity. 
  63. ^ Levitan. Elevated CO2 enhances nitrogen fixation and growth in the marine cyanobacterium Trichodesmium. 
  64. ^ Verspagen. Contrasting effects of rising CO2 on primary production and ecological stoichiometry at different nutrient levels. https://pure.knaw.nl/ws/files/1408909/5616_Verspagen_Postprint.pdf. 
  65. ^ Holding. Temperature dependence of CO2-enhanced primary production in the European Arctic Ocean. 
  66. ^ Benedetti, Fabio; Vogt, Meike; Elizondo, Urs Hofmann; Righetti, Damiano; Zimmermann, Niklaus E.; Gruber, Nicolas (2021-09-01). "Major restructuring of marine plankton assemblages under global warming" (in en). Nature Communications 12 (1): 5226. doi:10.1038/s41467-021-25385-x. ISSN 2041-1723. PMID 34471105. Bibcode2021NatCo..12.5226B.