አቅም
አቅም (Energy) በፊዚክስ ጥናት ሲተረጎም ያንድ ሰው፣ እንስሳ፣ ቁስ፣ ስራ የመሰራት ችሎታ ወይም ለውጥ የማምጣት ችሎታ ማለት ነው። አቅም የሚለካው በጁል (Jules) ነው።
ሳይንሳዊ አቅም
ለማስተካከልሳይንሳዊ አቅም በሁለት ይክፈላል
- ተንቀሳቃሽ አቅም (Kinetic energy)
- የምንለው አንድ ቁስ በመንቀሳቀሱ ምክያት ስራ ለመሰራት የሚያዳብረው አቅም ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ ድንጋይ ቢወረወር ያ ድንጋይ በንቅስቃሴ ላይ እያለ ጠርሙስ ቢያጋጥመው ያን ጠርሙስ የመስበር ስራ ያካሂዳል። በዚ ምክንያት የተወረወረ ድንጋይ ተንቀሳቃሽ አቅም አለው እንላለን።
- እምቅ አቅም (Potential energy)
- የምንለው ደግሞ አንድ ቁስ ወይም የቁስ ስርዓት በጉልበት ሜዳ ውስጥ ባለው አቀማመጥ ምክንያት በውስጡ የተከማቸ አቅም ነው። ለምሳሌ የመሬት ስበት በምድራችን ዙሪያ የመሳብ ጉልበት ሜዳ ፈጥሮ አለ። በዚህ ምክንያት አንድን ድንጋይ ከመሬት አንስተን ብንይዝ በዚያ ዲንጋይ ላይ እምቅ አቅም ይኖራል ምክናይቱም ድንጋዩን ስንለቀው ባለው እምቅ አቅም ምክንያት አንድን ጠርሙስ መስበር ይችላል።
አቅም አይጠፋም
ለማስተካከልከላይ እንዳየነው ሁለት አይነት የአቅም አይነቶች አሉ። በነዚህ ስር የሚተዳደሩ ሌሎች አይነቶችም አሉ። ለምሳሌ የ"ኮረንቲ አቅም"፣ የ"ማግኔት አቅም"፣ የ"ድምጽ አቅም"፣ ወዘተ.. ነገር ግን አንዱ አይነት አቅም ወደ ሌላ አቅም ሲቀየር ወይም አይጨምርም ወይም ደግሞ አይቀንስም። የአቅሙ መጠን ምንግዜም አንድ አይነት ነው። በሌላ ቋንቋ፦
ምንጊዜም አቅም አይፈጠርምም አይጠፋምም።
ምሳሌ
ለማስተካከል- ሲጀመር የአንድ ቁስ አቅም ተለካ እንበል። ሲለካ 50 ጁል ነው እንበል።
- እንበልና የዚህ እቃ አቅም እምቅ ነበር ነገር ግን በመንቀሳቀሱ ወደ ተንቀሳቃሽ አቅም ተቀየረ።
- በመጨረሻ የዚህ እቃ አቅም ተለካ።
በዚህ ጊዜ ሲጀመርና ሲያልቅ ያለው አቅም እኩል ሆኖ ይገኛል። ይኽውም 50 ጁል ነው ማለት ነው።
አዲሱ የ"አቅም አይጠፋም" ህግ
ለማስተካከልበአሁኑ ዘመን ሳይንቲስቶች አንድን ቁስ አካል ወደ አቅም በኑክልያር መበታተን እና ኑክሊያር መገጣጠም መለወጥ እንደሚቻል ደርሰውበታል። በዚህ ምክንያት የአቅም አይጠፋም ህጉ ይህን ጉዳይ ለማስተናገድ ሲባል የቁስና አቅም አይጠፋም ህግ ብለውታል።
የአቅም አይነቶች
ለማስተካከልከብዙ በጥቂቱ ...
አቅምን መለኪያ
ለማስተካከልከላይ እንደተገለጸው አቅም ይለካል። ይህም በቁጥር ይተመናል። የአቅም መለኪያ ዩኒት ጁል (J) ይባላል። አንድ ጁል ከአንድ ኒውተን ሜትር (1Nm) ወይም ( 1 kg m2 s−2) ጋር እኩል ነው።