ዳይኖፍላጅሌቶች ( በግሪክኛ δῖνος ዲኖስ “ተሽከርካሪ” እና በላቲንኛፍላጀለም “ጅራፍ፣ ግርፋት”) የሚል ትርጉም ያላቸው የጋራ ባህሪያት ኖሯቸው ዳይኖፍላጅላታ የተሰኘ ክፍለስፍን የተመሰረተላቸው ባለ ነጠላ ሕዋስ ውን ኑክለሳውያን ቡድን ናቸው።[1] እናም አብዛኛውን ጊዜ እንደ ፕሮቲስት ይቆጠራሉ።ዳይኖፍላጅሌቶች በአብዛኛው የባህር ፕላንክተኖች ናቸው፤ሆኖም ግን በለጋ ውሃማ መኖሪያዎች ውስጥም የተለመዱ ናቸው።ስብስባቸው ከባህር ወለል ሙቀት፣ ከጨዋማነት እና ከጥልቀት ጋር ተያይዞ ይለዋወጣል። ብዙ ዳይኖፍላጅሌቶች የብርሃን አስተጻምሮ ያካሂዳሉ፤ከዳይኖፍላጅሌቶቸ ትልቁ ክፍል ግን የብርሃን አስተጻምሮን እና አደን መመገብን(መዋጥ ወይም ወደውስጣቸ ማስገባት) ያጣመረ የአመጋገብ ስርአትያላቸው ናቸው። [2] [3]

ሴራሽየም ሂሩዲኔላ
ዳይኖፍላጅላታ

ከዝርያዎች ብዛት አንፃር፣ ዳይኖፍላጅሌቶች ከታላላቅ የባህር ውስጥ ውን ኑክለሳውያን ቡድኖች የሚመደቡ ናቸው፤ ሆኖም ግን ጉልህ በሆነ መልኩ ከባልጩት ዋቅላሚዎች ያንሳሉ። [4] አንዳንድ ዝርያዎች የባህር ውስጥ እንስሳት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፤ እናም በኮራል ሪፍ ስነህይወት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። ሌሎች ዳይኖፍላጅሌቶች ቀለም አልባ ሲሆኑ የፕሮቶዞአ አዳኞች ናቸው፤ጥቂት ዝርያዎች ደግሞ ጥገኛ ናቸው (ለምሳሌ ኦኦዲንየም እና ፊስቴሪያ)። አንዳንድ ዳይኖፍላሌቶች የሕይወት ዑደታቸው አካል የሆኑ ሲስት ወይም ዳይኖሲስት የሚባሉ የዕረፍት ደረጃዎች አሏቸው። ይህ ከተገለጹት 350 የለጋ ውሃ ዝርያዎች በ84ቱ ውስጥ እና ከባህር ውስጥ ዝርያዎች ከ10% በላይ በሆኑት ይከሰታል. [5] [6] ዳይኖፍላጅሌቶች ሁለት ልምጭቶች ያላቸው አልቪዮሌቶች ሲሆኑ ለባይኮንቶች እንደ ቅድመ አያቶች ናቸው።

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል
  1. ^ A classification of living and fossil dinoflagellates. Micropaleontology Special Publication. 7. Hanover PA: Sheridan Press. 1993. OCLC 263894965. 
  2. ^ Mixotrophy among Dinoflagellates. 46. 1999. 
  3. ^ Progress in Botany: Genetics Physiology Systematics Ecology. Springer. 
  4. ^ "How many species of algae are there?". Journal of Phycology 48 (5): 1057–63. October 2012. doi:10.1111/j.1529-8817.2012.01222.x. PMID 27011267. 
  5. ^ "A review of recent freshwater dinoflagellate cysts: Taxonomy, phylogeny, ecology and palaeocology". Phycologia 51 (6): 612–619. doi:10.2216/11-89.1. 
  6. ^ "Towards an Ecological Understanding of Dinoflagellate Cyst Functions". Microorganisms 2 (1): 11–32. January 2014. doi:10.3390/microorganisms2010011. PMID 27694774.