ጀምስ ፒስ
ኬኔዝ ጀምስ ፒስ (በእንግሊዝኛ፦ Kenneth James Peace)፣ ልደት (እ.ኤ.አ) ሴፕቴምበር 28፣ 1963 (መጋቢት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ.ም.)፣ ፔይስሌይ (በእንግሊዝኛ፦ Paisley)፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ፒያኖ ተጫዋች እና ቪዡዋል አርቲስት (የሥነ /ጥበብ ባለሙያ) ነው።
የሕይወት ታሪክ
ለማስተካከልጅምስ ፒስ[1][2] የተወለደው እንደ አውሮጳውያን አቈጣጠር (እ.ኤ.አ) ሴፕቴምበር 28፣ 1963 በፔይስሌይ፣ ስኮትላንድ (በእንግሊዝኛ፦ Scotland) ውስጥ ነው።[1] አብዛኛውን የልጅነት ጊዜውን ያሳለፈው በምዕራብ ስኮትላንድ በምትገኝ ትንሽ የባሕር ዳርቻ የጎብኚዎች መዳረሻ በሆነችው በሄለንስበርግ (በእንግሊዝኛ፦ Helensburgh) ውስጥ ነው። ከቤተሰቦቹ መካከል ብዙ ከያኒያን አሉ (ለምሳሌ፣ ጆን ማክጊ፣ በእንግሊዝኛ፦ John McGhie)። ከሙዚቃ አቀናባሪው ከፌሊክስ ባርንስ (በእንግሊዝኛ፦ Felix Burns) ጋርም ይዛመዳል።[1][3] ከስምንት ዓመቱ ጀምሮ የፒያኖ ትምህርትን ተምሯል። የመጀመሪያውን ሕዝባዊ ትእይንት ያደረገው፣ በአሥራ አራት ዓመቱ የስኮት ጃፕሊንን (በእንግሊዝኛ፦ Scott Joplin) ሙዚቃ በተጫወተ ጊዜ ነበር። ከዚያም ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ደምበርተን (በእንግሊዝኛ፦ Dumbarton) በሚገኘው የቅዱስ አንድሪው ቤተክርስቲያን ውስጥ የፒያኖ ተጫዋች ሆኖ ተሰየመ። በአሥራ ስድስት ዓመቱ፣ (አሁን የስኮትላንድ ሮያል ኮንስርቫቶር [በእንግሊዝኛ፦ Royal Conservatoire of Scotland] በሚባለው) በሮያል ስኮቲሽ የሙዚቃ እና የድራማ አካዴሚ ውስጥ በትምህርት ቤቱ ታሪክ በዕድሜ ትንሹ የሙሉ ጊዜ ተማሪ በመሆን መማር ጀመረ። እ.ኤ.አ በ1983 እ.ኤ.አ ከግላዝጎ (በእንግሊዝኛ፦ Glasgow) ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ (በእንግሊዝኛ፦ B.A.) ዲግሪ ተመረቀ።[4][5] በቀጣዩ ዓመት፣ የመንደልሰንን (በጀርመንኛ፦ Mendelssohn) ፒያኖ ኮንሴርቶ ቁጥር 1ን፣ ከአር.ኤስ.ኤ.ኤም.ዲ ኦርኬስትራ ጋር በመጫወት በሙዚቃዊ ትወና ዲፕሎማ አገኘ።[1] መደበኛ ትምህርቱን ከፈጸመ በኋላ፣ በፒያኖ ተጫዋችነቱ በጣም የሚፈለግ ሆኖ፣ ከ1988 – 1991 ድረስ በኤዲንቦሮ (በእንግሊዝኛ፦ Edinburgh) ውስጥ ኖረ።[1][3]
ጀምስ ፒስ በጀርመን (በጀርመንኛ፦ Deutschland)፣ ባድ ናውሐይም (በጀርመንኛ፦ Bad Nauheim)፣ ውስጥ ከ1991 – 2009 (እ.ኤ.አ) ኖረ።[6][7][8] እ.ኤ.አ ከ1998 ጀምሮ ታንጎ ሙዚቃን አጥንቶ፣ የራሱን በታንጎ ሙዚቃ የተፀነሰ የፒያኖ ቅንብር የያዘ፣ “ታንጎ ስኮትቲሽ” (በእንግሊዝኛ፦ Scottish Tango) የሚባል ሲዲ አዘጋጀ።[8][9] እ.ኤ.አ በ2002 የቪክቶሪያ የሙዚቃ አካዴሚ (በእንግሊዝኛ፦ Victoria College of Music) የክብር አባል ሆነ።[3][8] በዚያው ዓመት፣ በመስከረም ወር ወደ ሰሜን ጀርመን፣[[10] በኅዳር ደግሞ በሩቅ ምሥራቅ ውስጥ የሙዚቃ ድግስ ጉዞ አደረገ። በሆንግ ኮንግ ውስጥ የራሱን ታንጎ XVII ለመጀመሪያ ጊዜ ተጫወተ።[8][11][12] በቶክዮ ደግሞ የአይ ፒ.ዲ.ኤን (በእንግሊዝኛ፦ International Piano Duo Association) የክብር ሜዳሊያ ተሸለመ።[1][3][5][8][13]
በቀጣዮቹ ዓመታት የሙዚቃ ትእይንቶቹ በአውሮፓ ውስጥ ያተኮሩ ነበሩ። የራሱን ታንጎ በሚከተሉት ዋና ከተሞች ውስጥ አቀረበ፦ አምስተርዳም፣ አቴና፣[14] በርሊን፣[15] ብራሰልስ፣ ሄልሲንኪ፣ ሊዝቦን፣ ለንደን፣ ማድሪድ፣[16] ኦስሎ፣[17] ሬይክያቪክ፣[18] እና ቪየና።
በ2005 እ.ኤ.አ በፓሪስ ውስጥ ከሚገኘው «የሉቴሴ» አካዴሚዓለም አቀፍ ኅብረት (በፊረንሳይኛ፦ Internationale Académie de Lutèce) የወርቅ ሜዳሊያ ተሸለመ።[1][3] እ.ኤ.አ በ2008 ደግሞ የለንደን የሙዚቃ አካዴሚ (በእንግሊዝኛ፦ London College of Music) የክብር አባል ሆነ።[1]
በኤዲንብራ ውስጥ ለጥቂት ጊዜያት ከቆየ በኋላ፣[3] በቪስባድን (በጀርመንኛ፦ Wiesbaden)፣ ጀርመን፣ ውስጥ ለመኖር እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2010 ወደ ጀርመን ተመለሰ።[1][2] በዚች ውብ ከተማ የሐሳብ ቀስቃሽነት በራሱ ሙዚቃ ላይ አጫጭር ፊልሞችን እንዲሠራ አደረገው። ይህም “ኬ. ጀምስ ፒስ ኢን ቪስባድን” (በእንግሊዝኛ፦ K. James Peace in Wiesbaden) የተሰኘውን ፊልም ይጨምራል።[19][20]
ሽልማቶች እና ክብሮች
ለማስተካከል⁖ «የአግነስ ሚለር» ውድድር (በእንግሊዝኛ፦ Agnes Millar Prize for sight-reading) የመጀመሪያ ደረጃ ሽልማት። ግላዝጎ፣ 1983 (እ.ኤ.አ)[4]
⁖ እ.ኢ.ሲ ውድድር (በእንግሊዝኛ፦ Educational Institute of Scotland Prize for piano accompaniment)። ግላዝጎ፣ 1984 (እ.ኤ.አ)[4]
⁖ «ሲበለኡሲ» ወድድር (በእንግሊዝኛ፦ Sibelius Essay Prize)። 1985 (እ.ኤ.አ)[4]
⁖ በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ቅንብር ውድድር፣ ቲ.አይ.ኤም (በጣሊያንኛ፦ Torneo Internazionale di Musica)፣ ዲፕሎማ። ሮም፣ 2000 (እ.ኤ.አ)[1][2][5]
⁖ አይ.ቢ.ኤል.ኤ ፋውንዴሽን (በእንግሊዝኛ፦ IBLA Foundation)፣ ዲፕሎማ። ኒው ዮርክ፣ 2002 (እ.ኤ.አ)[1][2][5][13]
የሠራቸው ሥራዎች ዝርዝር
ለማስተካከል⁖ የማለዳ ፍቅር ዝማሬ (በእንግሊዝኛ፦ Aubade)
⁖ ሥነ ሥርዓት ሰልፍ ፩ (በእንግሊዝኛ፦ Ceremonial March No.1)
⁖ ሥነ ሥርዓት ሰልፍ ፪ (በእንግሊዝኛ፦ Ceremonial March No.2)
⁖ ዝምተኛ እምባዎች (በእንግሊዝኛ፦ Silent Tears)
⁖ የመኸር ወርቅ (በእንግሊዝኛ፦ Autumn Gold)[21]
⁖ የተዘነጉ ቅጠላት (በእንግሊዝኛ፦ Forgotten Leaves)
⁖ ዘለዓለማዊ ዝማሬ (በእንግሊዝኛ፦ Eternal Song)[1]
⁖ ለኦቦ እና ለፒያኖ ሶናታ (በእንግሊዝኛ፦ Oboe Sonata)
⁖ ለጆርጂያ (በጂዮርጅኛ፦ საქართველოსთვის)
ግጥሞች ፦ ታማሪ ጪክቫይድዝ፣ ዩራቢ ጪክቫይደዝ፣ ጀምስ ፒስ
⁖ የወደቀ ውሃ (በእንግሊዝኛ፦ The Waterfall)
⁖ ኢዲሊስ (በእንግሊዝኛ፦ Idylls)
⁖ ፳፬ ታኒጎዎች (በእንግሊዝኛ፦ 24 Tangos)[1][9][19][20]
⁖ ባላደ (በእንግሊዝኛ፦ Ballade)
የውጭ መያያዣዎች
ለማስተካከልSouvenir de Buenos Aires, Op.29 Nr.3 (ሶቬኒዬር ደ ቡይነስ አይረስ፣ ኦፕ. 29፣ ቍ. 3)፣ Youtube
ማጣቀሻዎች
ለማስተካከል- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ ቸ ኀ ነ ኘ Birgitta Lampert። “ዊዝ አውት ‘ፕሪክሊ’ ሳውንድስ”። Wiesbadener Tagblatt (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣ ፌብሩወሪ10 ቀን 2011 (እ.ኤ.አ)
- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ Julia Anderton። “ታንጎ ላይክ ኤ ቢተርስዊት ስቶሪ”። Wiesbadener Kurier (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣ 24 ማርች 24 ቀን 2010 (እ.ኤ.አ)
- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ Sabine Klein። “ማይ ሚዩዚክ ኢዝ ላይክ ማይሰልፍ - ቬሪ ሮማንቲክ”። Frankfurter Rundschau (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣ 1992 እ.ኤ.አ፣ ውጤት 254፣ ገጽ 2
- ^ ሀ ለ ሐ መ G. Müller። “ዘ ሶል ኦፍ ዘ ፒያኖ ዳንስስ ታንጎ”። Kulturspiegel Wetterau (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣ መይ17 ቀን 2001 (እ.ኤ.አ)
- ^ ሀ ለ ሐ መ Deutsche Nationalbibliothek (ዶይቼ ናሲዮናል ቢብሊዮቴክ)። “ጀምስ ፒስ”
- ^ “ጀምስ ፒስ”። FRIZZ (የጀርመን መጽሔት)። ጃንዩዌሪ 2012 (እ.ኤ.አ)፣ ገጽ 5
- ^ Manfred Merz። “ኤ ቪርቱዎሲክ፣ ሴንሲቲቭሊ ከለርድ ሮማንቲክ ወርልድ”። Wetterauer Zeitung (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣ ኖቬምበር 12 ቀን 1992 (እ.ኤ.አ)
- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ “ጀምስ ፒስ”። The Tango Times (ኒው ዮርክ መጽጤት)፣ 2002/2003። ውጤት 39፣ ገጽ 1፣2፣4 ኢና5
- ^ ሀ ለ National Library of Scotland (ናሽናል ላይብራሪ ኦፍ ስኮትላንድ)። “Tango escocés”።
- ^ La Cadena (የደች መጽሔት)። ሴፕቴምበር ቀን 2002 (እ.ኤ.አ)፣ ገጽ5
- ^ TangoTang (የሆንግ ኮንግ ጋዜጣ)። ኦክተውበር 8 ቀን 2002 (እ.ኤ.አ)
- ^ “ጀምስ ፒስ”። South China Morning Post (ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት)፣ ኦክተውበር 9 ቀን 2002 (እ.ኤ.አ)
- ^ ሀ ለ ይ.ፒ.ዲ.ኤ.፣ የሸሌማት ተሽላሚዎች 2002 (እ.ኤ.አ)
- ^ የኮንስርት ፕሮግራም ብሮሹር {Για σένα, Αγγεληκή}። ምርች 27 ቀን 2016 (እ.ኤ.አ)
- ^ Tangodanza (የደች መጽጤት)። ሙጤት 1/2002 እ.ኤ.አ
- ^ የስፔን ኮንስርት ጉብኝት “¡Feliz cincuenta cumpleaños!” (ሴፕቴምበር፣ 2013 እ.ኤ.አ)
- ^ Listen.no: Konsert: James Peace, Flygel. Munch Museum፣ ኦስሎ። ኦክቶብር 16 ቀን 2004 (እ.ኤ.አ)
- ^ Rikarður Ö. Pálsson። “Skozir Slaghörputangoár”። Morgunblaðið (በአይስላንድ ጋዜጣ)፣ ኦክቶበር 14 ቀን 2004 (እ.ኤ.አ)
- ^ ሀ ለ National Library of Scotland (ስኮትሽ ናሽናል ሊብራሪ). “K. James Peace in Wiesbaden”
- ^ ሀ ለ Deutsche Nationalbibliothek (ዶይቼ ናሲዮናል ቢብሊኦቴክ). “K. James Peace in Wiesbaden”
- ^ Schwäbische Post (ሽዌቢሸ ፖስት፣ የበጀርመን ጋዜጣ)። “ዘ ሳውንድ ኦፍ ዝ ቫዮሊን ሶርስ ኦቨር ዘ ኦርኬስትራ”። ጁን 4 ቀን 1994 (እ.ኤ.አ)