የራውንድኸይ ገነት ትርኢት

የራውንድኸይ ገነት ትርኢትጥቅምት 5 ቀን 1881 ዓም የተቀረጸ የዓለም መጀመርያው ተንቀሳቃሽ ፊልም እንደ ነበር ይታመናል።[1] ፊልሙን ያቀረጸው የፈረንሳይ ፈጠራ ፈልሳፊ ሉዊ ለ ፕረንስ ሲሆን ቦታው በራውንድኸይ ሰፈር ሊድስእንግላንድ በጆሰፍና ሳራ ውትሊ ቤት ግቢ «ኦክዉድ ግሬንጅ» ነበር።[2] የውትሊዎች ልጅ ኤልሳቤት የሉዊ ለፕረንስ ሚስት ነበረች፣ አዶልፍም የለፕረንሶች ልጅ ሲሆን በፊልሙ ከጓደኛው አኒ ሃርትሊ አጠገብ ይታያል። እንዳጋጣሚ ወ/ሮ ሳራ ውትሊ ከተቀረጸው 10 ቀን በኋላ አረፉ።[3]

የራውንድኸይ ገነት ትርኢት

ርዕስ በሌላ ቋንቋ Roundhay Garden Scene
የተለቀቀበት ዓመት 1881 ዓም
ያዘጋጀው ድርጅት
ዳይሬክተር ሉዊ ለ ፕረንስ
አዘጋጅ
ምክትል ዳይሬክተር
ደራሲ
ሙዚቃ
ኤዲተር ሉዊ ለ ፕረንስ
ተዋንያን አኒ ሃርትሊ
አዶልፍ ለ ፕረንስ
ጆሰፍ ውትሊ
ሳራ ውትሊ
የፊልሙ ርዝመት 2.11 ሴኮንድ
ሀገር እንግላንድ
ወጭ
ገቢ
የፊልም ኢንዱስትሪ
ድረ ገጽ


የፊልሙ ርዝመት 2.11 ሴኮንድ ብቻ ሲሆን ከ1881 ዓም ጀምሮ የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ወይም ጭፈራ በቀጥታ መመልከት የሚያስችል በመሆኑ ግሩም ነው። ባለድምጽ ፊልም ገና ስላልኖረ ይሄ ድምጽ-የለሽ ፊልም ይባላል።

ዋቢ ምንጮችEdit

የውጭ መያያዣዎችEdit

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Roundhay Garden Scene የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።