ድምጽ ማለት በአየር፣ በፈሳሽና በጠጣር ነገር ውስጥ የሚጓዝ የአየር ጫና ማእበል ነው። ሁሉም በቁስ አካል ውስጥ የሚጓዝ ማእበል ግን ድምጽ አይደለም። ለመሰማት፣ የሚንቀሳቀሰው ሞገድ አንደኛ በቂ ሃይል ሊኖረው ያስፈልጋል (የጩኸቱ መጠን) ፣ የሞገዱ ድግግሞሽ ደግሞ ከ12 ጊዜ በሰከንድ እስከ 20000 ጊዜ በሰከንድ መሆን አለበት። የድግግሞሹ መጠን በጣም ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ ከሆነ፣ ምንም ያክል የሞገዱ ሃይል ከፍተኛ ቢሆን፣ ድምጹ አይሰማም።

የሳይን ሞግድ ለተለያዩ ድግግሞሽ; የታችኞቹ ሞገዶች ከላይኞቹ የበለጠ ድግግም አላቸው፣ የግራፉ ግርጌ የሚወክለው «ጊዜ»ን ነው።