ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 8
- ፲፱፻፳፬ ዓ.ም. - የኤሌክትሪክ መብራትን እንዲሁም አምፑልን በመፍጠር የሚታወቀው አሜሪካዊው ቶማስ አልቫ ኤዲሰን በ ኒው ጀርሲ ክልል ዌስት ኦሬንጅ ላይ በተወለደ በ ፹፬ ዓመቱ አረፈ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - የአሜሪካውን ፴፭ኛ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ገድለሃል በመባል የተያዘው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ በዛሬው ዕለት ተወለደ። ኬኔዲ በሞቱ በሁለተኛው ቀን እሱም ተገደለ።
- ፲፱፻፸ ዓ.ም. - የምዕራብ ጀርመን ወታደራዊ ጸረ ሽብርታዊ ቡድን በሽብርተኞት ተጠልፎ ሞጋዲሹላይ ያረፈውን የሉፍትሃንሳ አውሮፕላን ካስገደዱት አራት ሽብርተኞች መኻል ሦስቱን በመግደል የተያዙትን ፹፮ ሰላማዊ ተሳፋሪዎች ነጻ አወጣ።
- ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. - በቀድሞው የምሥራቃዊ ጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ መሪ የነበሩት ኤሪክ ሆኔካ ከሥልጣን ወረዱ።