ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 6
- ፲፰፻፸፱ ዓ/ም - የእስራኤል የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉት ዴቪድ ግሪን ወይም ዴቪድ ቤንጎርዮን ተወለዱ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ የመጀመሪያዋን አቶሚክ ቦንብ አፈነዳች።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በጋማል አብደል ናስር ሞት ምክንያት በግብጽ አንዋር ሳዳት የአገሪቱ ፫ኛ ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የዋቢ ሸበሌ ሆቴል ድርጅት በደርግ መንግሥት ተወረሰ።
- ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በቫቲካን የተሰበሰቡ የዓለም ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳሳት፣ በ ፬፻ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ጣሊያናዊ ያልሆኑትን በ ፖላንድ የክራካው ካርዲናል የነበሩትን ካሮል ዮሴፍ ቮይትዋን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (ፖፕ) በማድረግ መረጡአቸው። ዳግማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ በተመረጡ በ ፴፫ ቀናቸው በድንገት በሞት የተለዩትን የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ቀዳማዊ ዮሐንስ ጳውሎስን በመተካት ፪፻፷፬ናው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነዋል።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን የኬፕ ታውን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ደቡብ አፍሪቃዊው ዴዝሞንድ ቱቱ የ ኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀባይነታቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - ስመ ጥሩው የእስራኤል ጄኔራል፤ እንዲሁም በአገሪቱ የመከላከያ ሚንስቴርነት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ማዕረግ የበቁት ሞሼ ዳያን በተወለዱ በ፶፮ ዓመታቸው በሞት ተለዩ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር የሱዳን ፕሬዚዳንት ሆኑ።