ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥር 14
ጥር ፲፬ ቀን፣
- ፲፰፻፲፮ ዓ/ም - በቀድሞዋ 'ጎልድ ኮስት' (አሁን ጋና) የአሻንቲ ብሔረሰብ ሠራዊት የእንግሊዝን ሠራዊት በውጊያ አሸንፈው በአፍሪቃአኅጉር፣ የነጭ ቅኝ ገዥ ሠራዊትን በማሸነፍ የመጀመሪያው ብሔረሰብ ሆኑ።።
- ፲፰፻፸፩ ዓ/ም - በዛሬዪቷ ደቡብ አፍሪካ በእንግሊዝ ሠራዊት እና በዙሉ ብሔረሰብ መኻል በተካሄደው የ'ኢሳንድልዋና'(Battle of Isandlwana) ውጊያ ዙሉዎች አሸናፊ ሆኑ።
- ፲፰፻፺፫ ዓ/ም - በታላቋ ብሪታኒያ እና አየርላንድ ንጉዛት ዙፋን ላይ ለ፷፬ ዓመታት የነገሡት ንግሥት ቪክቶርያ በተወለዱ በ ፹፪ ዓመታቸው አረፉ።