ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ግንቦት 5
- ፲፰፻፸፫ ዓ/ም - የፈረንሳይ ቅኝ ገዝዎች የተቃራኒ አመጸኞች ቡድን ከቱኒዚያ ተነስቶ በግዛታቸው አልጄሪያ ጥቃት አድርሷል በሚል መነሻ ቱኒዚያን ከወረሩ በኋላ በሰንደቅ ዓላማቸው ጥላ ሥር እንድትስተዳደር አስገደዷት።
- ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስ ብዙ ሺ ሕዝብ በተሰበሰበበት በ’ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ’ በተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ቆስለው ወደህክምና ተወሰዱ።
- ፲፱፻፹፩ ዓ/ም - በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ፣ የቲያናማን አደባባይ ላይ በተማሪዎች የተመራ የረሀብ አድማ ተጀመረ።
- ፲፱፻፺ ዓ/ም - ሕንድ ግንቦት ፫ ቀን ያፈነዳቸውን ሦስት የኑክሊዬር ቦንቦች አስከትላ በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለት ቦንቦች አፈነዳች። በዚህ ምክንያት የአሜሪካ እና የጃፓን መንግሥታት በሕንድ ላይ የምጣኔ ኃብት ዕቀባ እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።