ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ነሐሴ 11
- ፲፰፻፶ ዓ/ም - በብሪታኒያ ንጉዛት እና በአሜሪካ ኅብረት መኻል በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የተዘረጋውን አዲሱን የቴሌግራፍ መስመር በመመረቅ ንግሥት ቪክቶሪያ እና የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጄምስ ቡካነን የሰላምታ መልእክት ተለዋወጡ።
- ፲፱፻፴፬ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ልጅ ልዕልት ፀሐይ በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የብሪታኒያ ዋና መላክተኛ (Ambassador) ዳግላስ ራይት (Douglas A. H. Wright) በኢትዮጵያ እና በኬንያ መኻል ያለውን ድንበር ለመስማማት የተዘጋጀውን የውል ረቂቅ ለኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ አስረከበ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ ሽግግር የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የክብር ዘበኛ ሠራዊት አዛዥ የነበሩት ማዮር ጄነራል ታፈሰ ለማ በደርግ ተይዘው ታሠሩ። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነብሩት አቡነ ቴዎፍሎስ አዲስ በተዘጋጀው ረቂቅ ሕገ-መንግሥት ውስጥ በተካተቱ አንዳንድ አንቀጾች ላይ ቅዋሜ እንዳላቸው አስታወቁ።