ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 6
- ፲፰፻፶፯ ዓ/ም - በአሜሪካ የ ዕርስ በ ዕርስ ጦርነት የሕብረት ወገን ጄኔራል ዊሊያም ተኩምሰ ሸርማን የጆርጂያን ከተማ አትላንታን አቃጠለ።
- ፲፰፻፹፪ ዓ/ም - በብራዚል ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት፣ ንጉሠ ነገሥቱን ዳግማዊ ፔድሮን ከሥልጣን አውርደው አገሪቱን ሪፑብሊክ አደርጓት።
- ፲፱፻፲፫ ዓ/ም - የዓለም መንግሥታት ማኅበር የመጀመሪያ ስብሰባውን በጄኔቭ ከተማ አካሄደ።
- ፲፱፻፸፭ ዓ/ም - በሞስኮ የቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ፕሬዚደንት ሊዮኒድ ብሬዥኔቭ የቀብር ስነ ስርዐት ተፈጸመ።
- ፲፱፻፸፮ ዓ/ም - በቆጵሮስ ደሴት በቱርክ ብቻ ሉዐላዊነቷ የሚታወቅላት የሰሜን ቆጵሮስ ቱርካዊ ሪፑብሊክ ተመሠረተች።
- ፲፱፻፹፩ ዓ/ም- የፍልስጥኤም ብሔራዊ ሸንጎ ሉዐላዊ ነጻ የፍልስጥኤም ግዛት አወጀ።
- ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - በቻይና ሕዝባዊ ሪፑብሊክ ሁ ጂንታኦ የኮሙኒስት ቡድን መሪ ሆኑ።