ስሜን ቆጵሮስ (በይፋ፦ «የቱርክ ስሜን ቆጵሮስ ሪፐብሊክ»፤ ቱርክኛ፦ Kuzey Kıbrıs /ኩዘይ ክብርስ/) በቆጵሮስ ደሴት ላይ የምትገኝ አገር ናት።

ስሜን ቆጵሮስ - ቀይ

ሐምሌ 8 ቀን 1966 ዓም የቆጵሮስ ግሪኮች ወገን የቆጵሮስ መንፈቅለ መንግሥት ስላካሄዱ፣ ስለዚህ በ13 ሐምሌቱርክ ሥራዊት በስሜን ወረረ፣ ጦርነቱም ከጨረሰ በኋላ የቱርኮች ወገን አስተዳደር በስሜኑ፣ የግሪኮችም በደቡቡ ቀርተው ነበር። በ1967 ዓም ስሜኑ «የቱርክ ቆጵሮስ ፌዴራላዊ ግዛት» ሆነ፣ በ1976 ዓም «የቱርክ ስሜን ቆጵሮስ ሪፐብሊክ» ሆነ።

የቆጵሮስ ቱርኮች በ1965 ዓም የነበሩባቸው ሥፍራዎች፦ ሐምራዊ

ሆኖም ከቱርክ አገር በስተቀር፣ ከአንዳችም ሌላ አገር ምንም ዲፕሎማቲክ ተቀባይነት የለውም። በተረፈ ሌሎቹ አገራት በይፋ በደቡብ የሚገኘውን የቆጵሮስ ሪፐብሊክን ይግባኝ ይቀበላሉ።

ምጣኔ ሀብቱ በተለይ በቱሪስም ይመሰረታል፤ ቱሪስቶቹ ወይም በአየር ከቱርክ አገር፣ ወይም በመርከብ ይገባሉ። በግል ጀልባ (ያሕት) የሚገቡም አሉ። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ምርቶች የወተት ውጤቶች፣ ሎሚአረቄዶሮድንች ናቸው። ሕዝቡ ቱርክኛ ይናገራልና የእስልምና ተከታዮች ናቸው። ዋንኛው እስፖርት እግር ኳስ ነው። ባሕላቸው በጭፈራና በሙዚቃ፣ በሥነ ጥበብ፣ በአበሳሰል ወዘተ. እንደ ቱርክ አገር ባሕል ይመስላል።