ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 12
- ፲፬፻፸ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ በእደ ማርያም፤ የዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ልጅ በተወለዱ በ ሠላሳ ዓመታቸው፤ በነገሡ በአሥር ዓመታቸው ባልታወቀ ህመም ሞቱ። ልጃቸው ዓፄ እስክንድር ወይም ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ ተተክተው ነገሡ።
- ፲፰፻፸ ዓ/ም - አሜሪካዊው የሰገላዊ-ፈጠራ ሰው ቶማስ አልቫ ኤዲሰን ድምጽን መቅረጽና መልሶ ማሰማት የሚያስችለውን “ፎኖግራፍ” የተባለውን ፈጠራውን አሳየ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - የኢራን ሃይማኖታዊ-መሪ አያቶላ ኾሜኒ በአሜሪካ ላይ ያላቸውን የጥላቻ መልዕክት የራዲዮ ስርጭት ተከትሎ፤ በፓኪስታን ርዕሰ ከተማ እስላማባድ አክራሪ አመጸኞች የአሜሪካን ኤምባሲ በእሳት ሲያወድሙት አምሥት ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል።
- ፲፱፻፹፬ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት የግብጽ ተወላጅ የሆኑትን ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊን ለድርጅቱ ስድስተኛ ዋና ጸሐፊነት መረጣቸው።