ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሚያዝያ 20
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - የዛምቢያ የመጀመሪያ ፕሬዚደንት የነበሩት ኬኔዝ ካውንዳ ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን አብደል ማጂድ አል ቲክሪቲ በዚህ ዕለት አል አውጃ በሚባል ሥፍራ ተወለዱ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ የፋሺስት መሪ የነበረው ቤኒቶ ሙሶሊኒ ከነውሽማው ክላራ ፔታቺ ጋር በቀበሌ ታጣቂዎች ተይዞ በኮሎኔል ካሌሪዶ ከተረሸነ በኋላ አደባባይ ላይ ቁልቁል ተሰቀለ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሆለታ ጦር ትምሕርት ቤት ብዙ የውጭ እንግዶች በተገኙበት የሃያ አምስተኛ የልደት በዓሉ ተከበረ።
- ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊው ቡጢኛ ሙሐመድ አሊ ወደአገሪቱ ጦር ሠራዊት ገብቶ በቪየትናምጦርነት ላይ የማገልገል ግዴታውን እንዲወጣ ቢጠየቅም አሻፈረኝ አለ። የዚያኑ ዕለት የዓለም ቻምፒዮናነቱን ማዕረግ በኒው ዮርክ የአትሌቲክ ባለ ሥልጣን ተገፈፈ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የአገራቸውን አርበኞች የመሩትና ከነጻነት በኋላም የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሆነው ለ አሥራ አንድ ዓመታት ያገለገሉት ሻርል ደጎል በፈቃድቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በስዊድን፤ ፊንላንድ እና ኖርዌይ የሚገኙ የኑክሊዬር ምርመራ ማዕከላት ያልተለመደ የጨረር ጉዳት በከላ በምድር ጠፈር ላይ እንዳገኙ ባስታወቁ በሁለተኛው ቀን የሶቪዬት ኅብረት ባለ ሥልጣናት ቸርኖቢል የሚባለው የኑክሊዬር የመብራት ኃይል ማምረቻ አደጋ እንደደረሰበት ይፋ አደረጉ።