ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 27
- ፲፱፻፲፪ ዓ/ም - የሆላንድን ዓርማ ያዘለው ‘ኬ. ኤል. ኤም’ (KLM) የተባለው እና ከምሥረታው ጀምሮ እስካሁን ስሙንም ሆነ ዓርማውን ሳይቀይር በመቆየት አንደኝነትን ያስመዘገበው ዓየር መንገድ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - ልዑል ራስ ተፈሪ መኮንን በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እጅ ዘውድ ጭነው ንጉሥ ተፈሪ ተባሉ።
- ፲፱፻፳፬ ዓ/ም - የደቡብ አፍሪቃው ጳጳስ እና የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀባይ ዴዝሞንድ ቱቱ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - አምሥት ነባር የፈረንሳይ አየር መንገዶችን በማዋሐድ የአሁኑ ‘ኤየር ፍራንስ’ (Air France) ተመሠረተ።
- ፲፱፻፵፪ ዓ/ም - የቀድሞው የምሥራቅ ጀርመን ሪፑብሊክ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የሩሲያ የቀድሞ ፕሬዚደንት እና የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ቭላዲሚር ፑቲን በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - ናይጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - ኦማንየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓባል ሆነች።
- ፲፱፻፺፬ ዓ/ም - አፍጋኒስታን በ አሜሪካ ሠራዊት ተወረረች።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - ኤርትራዊው ዘፋኝ፣ ገጣሚ እና የሙዚቃ አቀናባሪ አብርሐም አፈወርቂ ቀይ ባህር ውስጥ ሰምጦ በተወለደ በ ፵ ዓመቱ ሞተ።