ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 15
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም ሐምሌ ፩ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የጄኔቫውን ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናን ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር አግኝቶ ፵፰ኛው አባል ሆኗል።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም - ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ (ዘብሔረዘጌ) በዚህ ዕለት በእሥራት ላይ በነበሩበት ጅረን በሚባል በጅማ ከተማ አቅራቢያ ባለ ቦታ በተወለዱ በ ፸፱ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም አየር ዠበብ (አውሮፕላን) አብራሪው ሰሎሞን ግዛው በዚህ ዕለት ተወለዱ።