ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሐምሌ 24
- ፲፮፻፲፩ ዓ/ም - የመጀመሪያዎቹ አፍሪቃውያን ”ተገዳጅ ሎሌዎች” ወይም ባሪያዎች በዩናይትድ ስቴትስ ጄምስ ታውን፣ ቨርጂኒያ የሚባል ሥፍራ ላይ ከመርከብ ወረዱ።
- ፲፯፻፺፫ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታንያን እና የአየርላንድን ንጉዛቶች በማዋሐድ የአሁኗን የታላቋ ብሪታንያና የሰሜን አየርላንድ ንጉዛት ያስፈጠረው ሕግ ጸደቀ።
- ፲፰፻፳፮ ዓ/ም - በጠቅላላው የብሪታንያ ንጉዛቶች “ተገሎሌ" ወይም ባርነትን የሚደመስሰው ሕግ ተደንግጎ ጸደቀ። ሆኖም ሠራተኛ ያልሆኑ ተገሎሌዎች ሕጉ በጸደቀ በአራት ዓመቱ በዚሁ ዕለት በ፲፰፻፴ ዓ/ም ነጻነታቸውን ሲያገኙ ሠራተኛ ተገሎሌዎች ደግሞ ስድስት ዓመት ቆይተው በዚሁ ዕለት በ፲፰፻፴፪ ዓ/ም ነጻ ወጡ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - በኮንጎ ሽብር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ አስከባሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሆነው ያገለገሉት ሌተና ጄኔራል ከበደ ገብሬ የሥልጣን ጊዜያቸውን በዚህ ዕለት አጠናቀቁ።