ዋዝንቢት
ዋዝንቢት የሦስት አጽቄ አይነት ነው። የፌንጣና የአንበጣ ዘመድ ነው። ሁለንተናው ትንሽ ለጥ ይላል፤ ረጃጅም አንቴኖችም አሉት።
ዋዝንቢት የሚታወቀው በሚያሰማው ድምጽ ነው። ድምጽ ማውጣትና ማሰማት የሚችለው አውራው ዋዝንቢት ብቻ ነው። የተባዕቱ ዋዝንቢት ክንፍ እንደ "ሚዶና ሞረድ" የሚመስል ፍርግርግ ነው። ክንፎቹን በማፋተግ ድምጽ ይፈጥራል፤ የድምጹ ቅላፄ እንደየ ዋዝንቢቱ ወገን ይለያያል። ሁለት ዓይነት የዋዝንቢት ዘፈኖች አሉ፤ የጥሪ ዘፈንና የመርቢያ ዘፈን ናቸው። የጥሪ ዘፈን ዓላማ አንስት ዋዝንቢ ለመሳብ ሲሆን ረጅምና ከፍተኛ ድምፅ ነው። ለመራባት ሲባል የሚዘፈነው ድምፅ አንስቲቱ እንስቲቱን ለማቅረብ ስለሆነ ቀስ ያለና ለስላሳ ነው። አንስት ዋዝንቢት መርፌ የሚመስል ረጅም የዕንቁላል መጣያ አላት።
በምድር ላይ 900 የሚያሕሉ የዋዝንቢት ዝርያዎች ይገኛሉ። አንዳንድ ዝርያ ሣርና ተክል ብቻ ሲበላ፣ ሌሎች ዝርዮች ደግሞ ነፍሳት ያድናሉ። ዋዝንቢት ሌሊት የሚነቃ ፍጥረት ነው። ብዙ ጊዜ ከፌንጣ ጋር ይመሳሰላል፣ በተለይ የመዝለያ እግሮቹ ከፊንጣ እግሮች አይለዩም።
በ1963 ዓ.ም. ዶ/ር ዊሊያም ከይድ ምርመራ አድርጎ አንዲት ተባይ ዝንብ ደግሞ በተባዕቱ ዘፈን እንደምትሳብ፤ ዕጯንም እንድታስቀምጥበት ቦታውን ለማወቅ እንደሚጠቅማት አገኘ። የመርባትን ድምጽ በመጠቀም የአስተናጋጇን ቦታ ለምታገኝ የተፈጥሮ ጠላት ይህች መጀመርያ ምሳሌ ሆነች። ከዚያ በኋላ ብዙ የዋዝንቢት ወገኖች ይህችን ተባይ ዝንብ ሲሸክሙ በምድር ላይ ተገኝተዋል።
በእስያ በተላይም በቻይና ዋዝንቢት ዝነኛ ለማዳ እንስሳ ሆኖ መያዙ እንደ መልካም እድል ይቈጠራል። የተያዘ ዋዝንቢት ሁሉ ማናቸውም አትክልት ወይም ሥጋ ቢሰጥ ይበላል። በአንዳንድ ባሕል ደግሞ ዋዝንቢት እንደ ምግብ ሊበላ ይችላል።
ወገኖች
ለማስተካከልከዕውነተኛው ዋዝንቢት አይነቶች መካከል አንዳንዶቹ እንዲህ ናቸው፦
- የቊጥቋጦ ዋዝንቢት
- ተራ ወይም የሜዳ ዋዝንቢት፤ ቡናማ ወይም ጥቁር፤ ስሙም "የሜዳ" ምንም ቢሆንም፣ አንዳንድ ወደ ቤት ይገባል።
- ባለቅርፊት ዋዝንቢት
- የጉንዳን ዋዝንቢት
- የመሬት ዋዝንቢት
- የዛፍ ዋዝንቢት ፦ አብዛኛው አረንጓዴ ናቸው ክንፉም በውስጡ የሚያሳይና ሰፊ ነው፣ በዛፍና በቊጥቋጦ ይበዛል።
- እንግዳ ዋዝንቢት
- ባለሠይፍ ጅራት ዋዝንቢት
ከዕውነተኛው ዋዝንቢት ጭምር፣ ከነዚሁ ውጭ አያሌ ሌላ የተዛመዱ ተሐዋስያን ወገኖች "ዋዝንቢት" ሊባሉ ይችላሉ፦
- የፍልፈል ዋዝንቢት
- ባለ ረጅም ክንድ ፌንጦ
- የዋሻ ዋዝንቢት (ደግሞ የግመል ዋዝንቢት ይባላል)
- የአሸዋ ዋዝንቢት
- የዊታ ዋዝንቢት - በኒው ዚላንድ የሚገኝ
- የየሩሳሌም ዋዝንቢት - በሜክሲኮ አካባቢ የሚገኝ
- የፓርክታውን ፕራውን - ከደቡብ አፍሪቃ የሚገኝ ወገን ነው።