ክስታኔ
ክስታኔ ("ክርስቲያን" ቀደም ሲል በምዕራባውያን ምንጮች ውስጥ Aymälläl በመባል ይታወቅ የነበረ ሲሆን፣ አይመለል የመጀመሪያዎቹ ክስታኔዎች የሰፈሩበት አገር እንደሆነ ይነገራል ) በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ በቀድሞው አጠራር በሸዋ ክፍለ ሃገር በአሁኑ በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ የሚገኝ ማህበረሰብ ነው። ክስታኔ፣ ጉራጌ በመባል በወል ከሚጠሩት የቤተ ጉራጌ ማህበረሰቦች ውስጥ አንዱ ሲሆን ሶዶ ጉራጌ እየተባለም ይጠራል። የክስታኔ ህዝብ ቋንቋ ክስታኒኛ ይባላል። ክስታኒኛ የደቡባዊ ኢትዮጵያ ሴማዊ ቋንቋዎች አካል ሲሆን የሶዶ የክስታኔ ተወላጆች መነጋገርያ (መግባቢያ) ቋንቋ ነው። የክስታኔ ተወላጆች በብዛት በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ የሚገኙ ሲሆን እንዲሁም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍላተ ሃገራት ይኖራሉ።