ክለብ ሳንድዊች
ክለብ ሳንድዊች
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች (ለ6 ሰው)
ለማስተካከል- 1 ኪሎ ግራም ዳቦ
- 3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
- 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) ማዮኔዝ ሶስ
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) ተቀቅሎ የተከተፈ የዶሮ ሥጋ
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተከተፈ ቲማቲም
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተከተፈ የሰላጣ ቅጠል
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- 3 በቁመቱ የተከተፈ ቃርያ
- 4 ተቀቅሎ በቁመቱ የተከተፈ ዕንቁላል
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በቁመቱ የተከተፈ ለስላሳ የበሬ ሥጋ
- 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በቁመቱ የተከተፈ ሞርቶዴላ
አዘገጃጀት
ለማስተካከል- 1. ጥሬ ዕቃዎቹን በሙሉ ከዳቦ በስተቀር ከማዮኔዙ ጋር ቀላቅሎ መለወስ፤
- 2. ዳቦውን በጐኑ በሦስት ማዕዘን በስሱ መቁረጥ፤
- 3. የእያንዳንዱን ቁራጭ ጠብሶ አንዱን ገጽታ በቅቤ ማውዛት፤
- 4. ሦስት የሾርባ ማንኪያ ዉሑድ ባንድ ቁራጭ የወዛ ገጽታ ላይ አድርጐ በቢላዋ እየተጫኑ መስተካከል፤
- 5. በላዩ አንድ ቁራጭ ዳቦ መደረብና ከዉሑዱ ሦስት የሾርባ ማንኪያ ጨምሮ ማስተካከል፤
- 6. ተጨማሪ አንድ ቁራጭ መደረብና ጫን፣ ጫን አድርጐ ማስተካከል፤
- 7. ዙርያውን በቀጭኑ በቢላዋ እየከረከሙ ማስተካከል፤
- 8. የተደራረበውን ዳቦ ከላይኛው ግራ ማዕዘን ጫፍ በመጀመር ቀኝ ማዕዘኑ ድረስ በቢላዋ መቁረጥ፤