3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተከተፈ የሲለሪ ግንድ
5 የቡና ስኒ (250 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
1 የሾርባ ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
10 መካከለኛ ጭልፋ (1 ኪሎ ግራም) የተከተፈ ካሮት
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተከተፈ ባሮ ሽንኩርት
8 የሾርባ ማንኪያ (200 ግራም) የገበታ ቅቤ
ቡኬጋርኒ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
ግማሽ ሊትር ወተት ወይም ክሬም
1 ኪሎ ግራም በትንንሹ የተቆራረጠ ዳቦ
3 ሊትር ነጭ የበሬ ወይም የበግ መረቅ (ቢፍ/ላምብ ኋይት ስቶክ)
ሩብ ሊትር ዘይት

አዘገጃጀት

ለማስተካከል
1. በወፍራም ብረት ድስት ቅቤውን ማቅለጥና ማሞቅ፤
2. ቀይ ሽንኩርት፣ ሲለሪ፣ ካሮትና ባሮ ሽንኩርቱን ጨምሮ በነጩ በደንብ ማብሰልና ዱቄቱን ጨምሮ ማማሰል፤
3. የቲማቲም ድልሁን መጨመር፤
4. በዝግታ መረቁን እየጨመሩ በማማሰል ጨውና ቁንዶ በርበሬውን ጨምሮ እንዲበስል ማድረግ፤
5. ቡኬጋርኒውን ጨምሮ ለአንድ ሰዓት ያህል ማብሰል፤
6. ቡኬጋርኒውን አውጥቶ ድስቱን ካወረዱ በኋላ ንፁህ ብረት ድስት ከሥሩ በማድረግ በአትክልት መፍጫ መፍጨት፤
7. ድስቱን ለግማሽ ሠዓት ለሰስ ያለ እሳት ላይ አብስሎ ማውረድ፤
8. ክሬም ወይም ወተቱን አፍልቶ በትኩሱ መጨመር፤
9. ዳቦውን በትንሹ በአራት ማዕዘን ቅርፅ ቆርጦ ዘይቱን አግሎ መጥበስ፤
10. ለገበታ ሲፈለግ የተጠበሰውን ዳቦ በላዩ ጨምሮ ማቅረብ፡፡