ካሮሉስ ማግኑስ
ካሮሉስ ማግኑስ (ታላቅ ካርል ወይም እንደ ዘመናዊ ፈረንሳይኛ ሻርልማኝ) ከ761 እስከ 806 ዓም. ድረስ የፍራንኮች ንጉሥ ነበረ። በተጨማሪ ከ766 ዓም ጀምሮ የሎምባርዶች ንጉሥ፣ ከ793 ዓም የ«ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት» መጀመርያው ቄሣር ሆነ።
እስከ 777 ዓም ድረስ በጥምቀት ሥርዓት ወደ ክርስትና የገቡት በጠቅላላ በፈቃደኝነትና በሰላም ነበር። በ777 ዓም ግን ካሮሉስ የሳክሶኖች ብሔር (በጀርመን የቀሩትን ሕዝብ) በግድና በዛቻ አስጠመቁዋቸው። እምቢ አንጠምቅም ከሚሉት አረመኔዎች ሳክሶኖች ብዙ ሺህ አስገደለ።