ኩክ ደሴቶች
ኩክ ደሴቶች Cook Islands በፓሲፊክ ውቅያኖስ የሚገኝ የኒው ዚላንድ ራስ-ገዥ ደሴቶች አገር ነው።
ኩክ ደሴቶች |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: Te Atua Mou E | ||||||
ዋና ከተማ | ኣቫሩኣ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | እንግሊዝኛ ኩክ ደሴቶች ማዖሪኛ |
|||||
መንግሥት {{{ ንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ፪ኛ ሄንሪ ፐና |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
240 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት የ2011 እ.ኤ.አ. ቆጠራ |
21,000 14,974 |
|||||
ገንዘብ | የኒው ዚላንድ ዶላር ኩክ ደሴቶች ዶላር |
|||||
የሰዓት ክልል | UTC –10 | |||||
የስልክ መግቢያ | +682 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .ck |
ደሴቶቹ መጀመርያ በእስፓንያ መርከበኞች በ1587 ዓም ተዘገቡ። የክርስትና ሰባኪዎች ከ1813 ዓም ጀምሮ ደርሰው የኗሪዎቹ ብዛት የክርስትና ምዕመናን ሆነዋል። በ1880 ዓም የፈረንሳይ ቅኝ አገር እንዳይሆኑ ፈርተው በራሳቸው ልመና በዩናይትድ ኪንግደም ጥብቅና ሥር ገቡ፤ በ1893 ዓም ጥብቅናው ወደ ኒው ዚላንድ ተዛውሮ እስካሁን ድረስ ከኒው ዚላንድ ጋር ተባባሪነት አላቸው። ሕዝቡ ግን ምንጊዜም በተግባር ራስ ገዥ ሆነዋል።
ይፋዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ እና የኩክ ደሴቶች ማዖሪኛ ናቸው፤ ፑካፑካኛ ደግሞ ይነገራል።
ትንሽ ኮኮነት፣ ፓፓያ፣ ሎሚ፣ ቡና፣ ወዘተ. ለአለም ገበያ ይመረታሉ። በባህላዊ ሥነ ጥበብ፣ የእንጨት እጅ ሥራዎች፣ የሽመና ዕቃዎች፣ የሽመና ባርኔጣ፣ ትርዒት የሚያሳይ ድሪቶ፣ ወዘተ. ይሠራሉ። ራግቢ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ጨዋታ ነው። ባህላዊ ጭፈራዎች አሉ።
በኩክ ደሴቶች አበሳሰል ስምንት-እግር፣ ዛጎል ለበስ፣ የአሳማ ግልገል፣ የፖሊኔዥያ አሮውሩት፣ ጎደሬ ይበላሉ። ለቅመሞች ዝንጅብል፣ ሎሚ፣ በሶብላ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ኮኮነት ይጨመራሉ። በምግብ አሠራሮቹ መካከል፦
- ሩካው - የገደሬ ቅጠል በኮኮነት ወጥና ሽንኩርት
- ኢካ ማታ - ጥሬ አሣ በሎሚ ተዘፍዝፎ በኮኮነት ቅባት
- ፖኬ - በሙዝና በኮኮነት ወተት ወይም በፓፓያ የሚሠራ ጣፋጭ
አሉ። የአምበሾክ፣ የብርቱካንና የማንጎ ጭማቂዎች ይጠጣሉ፣ እንዲሁም የኮኮነት ውሃ፣ ቢራ፣ ቡና የሚወደዱ መጠጦች ናቸው።