እርካብ
እርካብ (ወይም ርካብ፣ ረካብ) ፈረስን የሚጋለብ ሰው እግሩን ያኖረበት፣ ለኮርቻ በጥብጣብ የሚያያዝ ቀለብቶ መዋቅር ነው።
ይሄ ፈጠራ ለፈረሰኞች እጅግ ጠቃሚ የመጋለብ ዘዴ አስቻለ። እርካቡ በእስያ በ200 ዓክልበ አካባቢ ከተለማ ጀምሮ ጥቅሙ እየተስፋፋ፣ እርካቦችን የጠቀሟቸው ፈረሰኞችና ሥራዊቶቹ እርካብ በሌላቸው ኃያላት ላይ የሚለታሪ ጥቅም ነበራቸው። ምክንያቱም የሚጋለበው ሰው ኮርቻ ውስጥ ሲቀመጥ በይበልጥ ወደ ጎን ማዘንበል ስለሚችል፣ እንዲሁም በይበልጥ በጦሩ (ወይም በሰይፉ) ኃይለኛ ምታት ማቅረብ ስለሚቻለው ነው። በተጨማሪ ከፈረሱ ጀርባ መውደቁ ወይም መጣሉ እንዳይደርስበት በመርዳቱ ጥቅም ይሰጠዋል። ስለዚህ በአንዳንድ የታሪክ መምኅር አስተሳሰብ ይሄ ፈጠራ አይነተኛ ወይም አብዮታዊ ሚና አጫውቷል።
ስም
ለማስተካከልየቃሉ መንስኤ ከአረብኛ ሪካብ ሲሆን ይህ ከጋራ ጥንታዊ የሴማዊ ቋንቋዎች ሥር «ረ ከ በ» («መሳፈር») ነው። ይህም ሥር አሁንም በ«መርከብ» እንዲሁም በ«ሩካቤ» ይታያል።
መስፋፋት
ለማስተካከልየእርካብ መነሻ በሕንድ አገር ይመስላል። በዚያ አገር የፈረሰኞች ልማድ ባዶ እግር ለመጋለብ ነበር። ምናልባት በ200 አክልበ. አካባቢ አንዳንድ ፈረሰኛ አውራ እግር ጣቱን በቆዳ ቅንዲላ ውስጥ አድርጎ ጥብጣቡ ለኮርቻው ይታሥር ነበር። ደንበኛ እርካብ በእርግጥ ከሥነ ቅርስ ምስሎች የታወቀው በቻይና ከ314 ዓ.ም. ነው። በ470 ዓ.ም. እርካብ በቻይና ውስጥ በሰፊው ይጠቀም ነበር። ከ550-600 ዓ.ም. ግድም ጀምሮ ከእስያ ወደ አውሮፓ የወረሩት ብሔሮች እንደ አቫሮች የእርካብ ጥቅም ወደ አውሮጳ አስገቡ። በቅርብ ከዚህ በኋላ የቢዛንታይን መንግሥት ፈረሰኞች ፈጠራውን ከአቫሮች ተምረውት ለሥራዊታቸው አስገቡት። ከቢዛንታይኖችም ዘዴው ለዓረቦች ተላለፈ። ከአቫሮችም የእርካብ እውቀት ለመካከለኛና ምዕራብ አውሮፓ ተስፋፋ።
አቫሮች ከወረሩ በፊት የአውሮፓ ሥራዊቶች በጥቂት ፈረሰኞች ቢጠቀሙ፣ ወታደሮች በተለይ እግረኞች ነበሩ። የእርካብ ጥቅም በአውሮፓ ከተስፋፋ በኋላ፣ ሥራዊቶቹ በብዛታቸው ከፈረሰኞች ተሠሩ። በኢንግላንድ ግን እስከ 1058 ዓም. ድረስ አብዛኛው ሥራዊት እግረኞች ሲሆኑ በሄስቲንግስ ውግያ ከኖርማንዲ በደረሱት በፈረሰኞች ሥራዊት ተሸነፉ።