ኤሪዱ (ወይም ኤሪዱግ / ኡሩዱግ፣ ከሱመርኛ ኤሪ-ዱጋ «ጥሩ ከተማ») ከዑር ወደ ደቡብ-ምዕራብ 7 ማይል የራቀ ጥንታዊ ከተማ ነበረ። በሱመርመስጴጦምያ በመስጊዶች ዙሪያ ከተመሠረቱት ከተሞች አንዱ ሲሆን ከሁላቸው ወደ ደቡብ ተገኘች።

ሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ ኤሪዱ የዓለሙ መጀመርያ ከተማ ነበረ። እንዲህ ሲል፦

«[ናም]-ሉጋል አን-ታ ኤድ-ዴ-አ-ባ
[ኤሪ]ዱ ናም-ሉጋል-ላ»
«ንጉስነት ከሰማይ ሲወርድ፣
ንጉስነቱ በኤሪዱ ነበረ።»

በሱመር አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ከማየ አይህ ቀድሞ ከተሠሩት 5ቱ ከተሞች አንዱ እንደ ነበር ተባለ። ለመሆኑ በሥነ-ቅርስ ረገድ የሱመር መጀመርያ ከተማ ሆኖ ይመስላል። ሲገነባ ኤፍራጥስ ወንዝ ወደ ፋርስ ባሕር ወሽመጥ ወደብ በሚፈስስበት ስፍራ እንደሆነ ቢታሥብም ዛሬ ግን በአሸዋ ጥርቅም ምክንያት ባሕሩ ከቦታው በጣም ይርቃል።

ኤንኪ (አምላክ ወይም ጣኦት) ቤተ መቅደስ በኤሪዱ 'ኤ-አብዙ' ተባለ። የኤንኪ ሚስት የኒንሁርሳግ ቤተ መቅደስ 'ኤ-ሳጊላ' ደግሞ በአካባቢው ነበረ።

መምህርዋ ኬት ፊልደን እንደምትለው፣ «ከ2050 ክ.በ. ገዳማ በፊት ከተማው ዝቅ ብሎ መኖርያ እንደሆነ ትንሽ ምልክት ብቻ አለ። ንጉስ አማር-ሲን (2055-2047 ክ.በ. ገዳማ) ካልጨረሰው መስጊድ በታች 18 የጡብ ቤተ መቅደሶች አሉ።»

በኋላ ዘመን በአሦር ቤተ መንግሥት ልዩ ህኪሞች ስለ በሽታ ጠንቆች ህክምና ለማወቅ የኤሪዱ ጥንታዊ ጥበብ መማር ነበረባቸው።

በአፈ ታሪክ

ለማስተካከል

በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር በኩል፣ ኤሪዱ የመጀመርያ ነገሥታት ከተማ ተብሎ እንዲህ ይቀጥላል፦

በኤሪዱ፣ አሉሊም ንጉሥ ሆኑ፤ ለ28,800 አመታት ገዙ። አላልጋር ለ36,000 አመታት ገዙ። 2ቱ ንጉሶች ለ64,800 አመት ገዙ። ከዚያ ኤሪዱ ወደቀና ነጉስነቱ ወደ ባድ-ቲቢራ ተወሰደ።

(የነገሥታት ዝርዝሩ ከጥፋት ውኃ በፊት ለገዙት ነገሥታት እጅግ ረጅም ዘመን ይሰጣቸዋል።)

ስለ ኢናና (የኡሩክ ከተማ ሴት አምላክ) ደግሞ አንዳንድ ትውፊት ይተረክ ነበር። የሥልጣኔ ስጦታ ለመቀበል ወደ ኤሪዱ መጓዝ እንደ ነበረባት ተባለ። ኤንኪ በመጀመርያ የሥልጣኑን ምንጭ ለመመለስ ቢሞክርም፣ ኋላ ግን ኡሩክ የአገሩ መሃል መሆኑ ተስማማው።

አንዳንድ የባቢሎን ጽሕፈት ደግሞ አምላካቸው ማርዱክ ኤሪዱን እንደ 'መጀመርያ ቅዱስ ከተማና የአማልክት መኖርያ' ሆኖ እንደ ፈጠረው ይላል።

የመምህር ዴቪድ ሮህል ኅልዮ በጣም ትኩረት ይስባል። በሱ አሳብ ዘንድ፣ ኤሪዱ ከዑር ወደ ደቡብ መጀመርያይቱ ባቢሎን ነበረችና የባቢሎን ግንብ ሥፍራ በኋለኛው ባቢሎን ሳይሆን እዚህ እንደተገኘ ያምናል። ምክንያቶቹም፦

  1. የኤሪዱ ቤተ መቅደስ (ግንብ) ፍርስራሽ ከሌሎቹ ይልቅ በጣም ረጅምና ጥንታዊ ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ እንደ ተገለጸ ያልተጨረሰውን የባቢሎን ግንብ ይመስላሉ።
  2. በሱመርኛ ጽሕፈት፣ የኤሪዱ ቁልምጫ ስም «ኑን-ኪ» (ታላቁ ሥፍራ) ነበረ። በኋለኛ ዘመን ደግሞ ይህ «ኑን-ኪ» ማለት ባቢሎን ከተማ ነበረ።
  3. ቤሮሥሥ ነገስታት ዝርዝር ትርጉም በግሪክ (200 ክ.በ. ገዳማ) ሳለ፣ 'ንጉስነቱ ከሰማይ የወረደበት' ሲል በ'ኤሪዱ' ፈንታ 'ባቢሎን' ብሎ ይጻፋል።
  4. ከዚህ በላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ናምሩድ የሚለው አዳኝ ሆኖ ኦሬክ (ኡሩክ) እና ባቢሎን እንደ ሠራ ይመሰክራል። በሱመር ትውፊት ደግሞ ንጉሱ ኤንመርካር ይገኛል። '-ካር' አዳኝ ማለት ይሁንና በዋና ከተሞቹ በኡሩክና በኤሪዱ ቤተ መቅደሶች እንደ ሠራ ይተረካል።

«ባቢሎን» (ባብ-ኢሊ) ማለት የኤሪዱ መጠሪያ እንደ ነበር የሚል ማስረጃ በሌሎችም ጥናቶች አለ።[1]

የውጭ መያያዣዎች

ለማስተካከል

ዋቢ መጻሕፍት

ለማስተካከል
  • Margaret Whitney Green, Eridu in Sumerian Literature, PhD dissertation, University of Chicago, 1975.
  • A. Leo Oppenheim, Ancient Mesopotamia: Portrait of a dead civilization.
  • Gwendolyn Leick, Mesopotamia: The invention of the city.
  1. ^ "Babylon as a Name for Other Cities..." Archived ጁላይ 30, 2012 at the Wayback Machine p. 25-33. (እንግሊዝኛ)