ወደ * ECTV ኢሲቲቪ የአማርኛ ቴቪ በአሜሪካን ዊኪፔድያ እንኳን ደኅና መጡ!

ዊኪፔድያ የተሟላ፣ ትክክለኛ እና፡ ነጻ መዝገበ ዕውቀትን በብዙ ቋንቋዎች ለማቅረብ የሚጥር የትብብር ሥራ ውጤት ነው። ይህ የአማርኛው ዊኪፒዲያ ጥር፡ 18 ቀን 1996 ዓመተ ምሕረት (27 January 2004 እ.ኤ.አ.) የተጀመረ ሲሆን 15,308ጽሑፎችን፡ አካቶ ይዟል።

ይህን መዝገበ እውቀት የተሟላ ለማድረግ አሁን ካሉት መጣጥፎች በብዙ ዕጥፍ የሚበልጡ ጽሑፎች ያስፈልጉናል። የፕሮጀክቱ ጀማሪዎች እና አንቀሳቃሾች ፕሮጀክቱን በመምራት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ርእሶች መጣጥፍ በማዘጋጀትም ጭምር እየተሳተፉ ነው። እባክዎን እርስዎም በአማርኛ መጻፍ ከቻሉ፣ በሚፈልጉት ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ ጽሑፎችን በማቅረብ ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት አስተዋጽኦ ያድርጉ። ይህ ሥራ ወደፊት በጣም ትልቅና ጠቃሚ የዕውቀት ምንጭ እንደሚሆን ተስፋ አለን።

ዊኪፔድያ የጋራ ነው። ማንኛውም ሰው ለዚህ መዝገበ ዕውቀት ተዋጽዖ ሊያደርግ ይችላል። ጽሑፍ ለማቅረብ ወይም በአርትዖት ሥራ ለመሳተፍ ዘዴው በጣም ቀላል ነው። ጽሑፍ ለማቅረብም ሆነ የጽሑፍን ስሕተት፣ የፊደል ግድፈት (ታይፖ)፣ ወዘተ. ለማስተካከል፤ ወይም የጽሑፍ ማከያ ለማቅረብ ማድረግ ያለብዎት በዚያው ገጽ የኅዳግ ጥግ ያለውን "ይህን ገጽ ለማዘጋጀት" የሚለውን መጫን ብቻ ነው።

በቀይ ቀለም የሚታዩ ቃላት ገና ያልተጻፉ አርእስትን ይጠቍማሉ። በእነዚህም ሆነ በሌሎች ርእሶች ላይ መጣጥፍ ለማቅረብ ይችላሉ። ሥራዎ ያልተጠናቀቀ መስሎ ቢሰማዎ እምብዛም አይጨነቁ፤ አንዳችን የሌላችንን ስራ (ጽሑፍ) በማረም በጋራ በጣም ጠቃሚ መጣጥፎችን ማበርከት እንችላለን።

በተጨማሪ የእርዳታ ገጽ ላይ የቀረበውን ማስታወሻ አንብበው ማንኛዉንም ጽሑፍ ለማቅረብ ከአሁን ጀምሮ ይሞክሩ። ሙከራ ለማድረግ ቢፈልጉ፣ በማንኛውም ጊዜ ወደ መፈተኛው ቦታ መሻገር ይችላሉ።

የተሳትፎዎትን መጀመርያ መጣጥፍ ከእንግሊዝኛው ዊኪፔድያ በመተርጐም ማቅረብ ይቀልዎት ይሆናል። እጅግ ብዙ ትርጕም መጣጥፎች ቢኖሩን ለአማርኛው ዊኪፒዲያ ማደግ መልካም መንገድ ይጠርጋሉ።

ዛሬ ማክሰኞ፣ [[ውክፔዲያ:የቀን መለወጫ/30 ኤፕሪል]] ቀን 1999 ዓመተ ምኅረት ነው።
የዛሬ ቀን (እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር) 30 ኤፕሪል, 2024 ነዉ።