አበራ ለማ ( Aberra Lemma) የተወለደው በ1943 ዓ.ም. ፍቼ ሰላሌ ውስጥ ነው። እድገቱ ወሊሶንና አዲስ አበባን ያካትታል። ካገራችን ገጣሚያንና አጫጭር ልቦለድ ጸሓፊዎች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ጥናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማዕርግ ተመራቂ ነው። ሙያው በጋዜጠኝነት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች ሠርቷል። ከጦር ግንባር ጋዜጠኝነት እስከ ኪነጥበባት ዘርፎች ሃያሲነት ዘልቋል።

እስከ ሰማኒያዎቹ አሠርት አጋማሽ ድረስ፥ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ዋና ጸሃፊ ሁኖ አገልግሏል። ዛሬ የኖርዌይ ነዋሪ ነው። በኖርዌይ ደራስያን ማኅበር ብቸኛውና የመጀመሪያው ጥቁርና ባፍ መፍቻ ቋንቋው የሚጽፍ አባል ደራሲ ነው። በዚህ ማኅበር ውስጥ የዓለም አቀፍ ኮሚቴው የረዥም ዘመን አባል በመሆንም ይታወቃል። ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህንንና (1997) ስዊድናዊ/ኤርትራዊ የሆነውን የአስመራውን እስረኛ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅን (2009 እ.ኤ.አ.) ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ሽልማት እንዲሸለሙ በእጩነት አቅርቦ ማሸለሙም ይታወሳል።


የተለያዩ ሽልማቶችን በኢትዮጵያና በውጭ አግኝቷል፡፡

1. ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ በ2013 ዓ.ም. የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ምርጥ ጋዜጠኛ

2. የኢሕደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የክብር ሜዳይ ሽልማት፣ በሥነ ጽሑፍ አስተዋጽኦ፣ 2013 ዓ.ም. 3. በ1981 ዓም በሥነ ግጥም ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ፣ ሰሜን ኮርያ 4. እአአ በ2010 ዓም በዩዲኔዝ ኢጣሊያ፣ የበጎ ሰውነት የMother Land Ethiopia የዋንጫ ሽልማት

*****ከአበራ ለማ የታተሙ ሥራዎች የሚከተሉት ይጠቀሳሉ።

Ø 1967 ኩል ወይስ ጥላሸት፣ የግጥም መድብል፣

Ø 1974 ሽበት፣የግጥም መድብል፣

Ø 1975 ሕይወትና ሞት፣የአጫጭር ልቦለዶች መድብል፣

Ø 1976 ሞገደኛው ነውጤ፣ ኖቭሌት፣

Ø 1978 አባደፋር፣ከሌሎች ደራስያን ጋር… ስብስብ፣

Ø 1978 ጽጌረዳ ብእር፣ከሌሎች ገጣሚያን ጋር… ስብስብ፣

Ø 198ዐ የማለዳ ስንቅ፣ያጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞች መድብል፣

Ø 198ዐ መቆያ፣ያጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞች መድብል፣

Ø 1981 ትዝታን በጸጸት፣ የቻይና ያጫጭር ልቦለዶች ትርጉም… በጋራ፣

Ø 1994 አውጫጭኝ፣ የግጥም መድብል፣

Ø 1994 ሙያዊ ሙዳዬ ቃላት፣ ኢልቦለድ…የቋንቋ ጉዳይ፣

Ø 1999 የእውቀት ማኀደር፣ ኢልቦለድ…

Ø 2ዐዐ2 እውነትም እኛ፣ የግጥም ስብስብ በዲቪዲ፣

Ø 2ዐዐ3 ጥሎ ማለፍ፣ ታሪካዊ ልበለድ

Ø 2006 ሽፈራው- ሞሪንጋ፣ ኢልቦለድ

Ø 2ዐዐ8 ቅንጣት- የኔዎቹ ኖቭሌቶች

_ 2013 ኩርፊያና ፈገግታ፣ የግጥም መድብል

Ø 1981 G.C.የኢትዮጵያውያን ገጣሚያን ሥራዎች ወደ ራሽያ ቋናቋ የተተረጎመ. በጋራ

Ø 2003 G.C. ULIKE HORISONTER (ኖርዌጂያንኛ ግጥሞች)፣ በጋራ

Ø 2017 G.C. ENKETRØSTREN (በኖርዌጂያን ኖቭሌቶች)

Ø 2014 G.C. TIME TO SAY NO፣ (የእንግሊዝኛ ግጥሞች) በጋ

-2014 ትውስብ - ያጫጭር ልቦለዶችና ኖቭሌቶች ስብስብ