አራዳ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ካሉት ዐሥሩ ክፍለ ከተሞች ውስጥ አንዱ ነው። እስከ እ.ኤ.አ 2011 ባለው መረጃ መሠረት የሕዝብ ብዛቱ 225,999 ነው።
አራዳ የሚገኘው በአዲስ አበባ በስተሰሜን አቅጣጫ ላይ ሲሆን ጉለሌን፣ የካን፣ ቂርቆስን፣ ልደታን እና አዲስ ከተማን ያዋስናል።