ናራም-ሲንአሹር ንጉሥ ነበር። ምናልባት 1782-1730 ዓክልበ. አካባቢ ገዛ። የ2 ፑዙር-አሹር ልጅና ተከታይ ይባላል።

ሃቲ የነበሩት ካሩም (የንግድ ጣቢያዎች) አስቀጠለ። ወደ ዘመኑ መጨረሻ ግን (ምናልባት 1745 ዓክልበ. አካባቢ) የካሩም ንግድ ለ30 ዓመት ያህል እስከ ሻምሺ-አዳድ ዘመን ድረስ ተቋረጠ።

የናራም-ሲን ልጅ 2 ኤሪሹም ተከተለው።

የዓመት ስሞች

ለማስተካከል

የያንዳንዱ አሦራዊ ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ። ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ።[1]

«የማሪ ሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል» የተባለው ሰነድ ከዚህ ዘመን ጀምሮ የሊሙ ስምና ተጨማሪ የዓመት ድርጊቶች ይሰጣል።[2] እነዚህ የጎረቤቱ ነገሥታት አሚኑም (የኡኒና ንጉሥ)፣ 2 ኢፒቅ-አዳድ (የኤሽኑና ንጉሥ)፣ 1 ሻምሺ-አዳድ፣ እና የሌሎች ዘመቻዎች ይዘግባሉ። ይህም በታች ይመለከታል።

የአሦር ነገሥታት ዝርዝር ደግሞ በዚህ ናራም-ሲን ዘመን የኢላ-ካብካቡ ልጅ ፩ ሻምሺ-አዳድ ወደ «ካርዱኒያሽ» (ባቢሎን) እንደ ሄደ፤ በኋላም በ1723 ዓክልበ. ከባቢሎን ወጥቶ ኤካላቱምን እንደ ያዘ፣ በ1720 ዓክልበ. አሹርንም ይዞ የአሦር ንጉሥ እንደ ሆነ ይዘግባል።

1782 ዓክልበ. - ኢናያ፣ አሙራያ ልጅ
1781 ዓክልበ. - ሹ-ሲን፣ ባቢሉም ልጅ
1780 ዓክልበ. - አሹር-ማሊክ፣ አላሁም ልጅ
1779 ዓክልበ. - አሹር-ኢሚቲ፣ ኢሊባኒ ልጅ
1778 ዓክልበ. - ኤና-ሲን፣ ሹ-አሹር ልጅ
1777 ዓክልበ. - አኩቱም፣ አላሁም ልጅ - «<...> ያዘ።»
1776 ዓክልበ. - ማጺሊ፣ ኢሪሹም ልጅ
1775 ዓክልበ. - ኢዲን-አሁም፣ ኩዳኑም ልጅ
1774 ዓክልበ. - ሳማያ፣ ሹበሉም ልጅ - «አሚኑም ሻዱፑምን ያዘ።»
1773 ዓክልበ. - ኢሊ-አሉም፣ ሱካሊያ ልጅ - «ሲን-አቡም ሲትን ምድር ያዘ።»
1772 ዓክልበ. - ኤናማኑም፣ አሹር-ማሊክ ልጅ
1771 ዓክልበ. - ኤናም-አሹር፣ ዱነያ ልጅ - «ኢፒቅ-አዳድ ያባቱን ቤት ገባ።»
1770 ዓክልበ. -ኤና-ሲን፣ ሹ-እሽታር ልጅ
1769 ዓክልበ. - ሃናናሩም - «አሚኑም ኢፒቅ-አዳድን ድል አደረገው።»
1768 ዓክልበ. - ዳዲያ / ካፓቲያ - «ኢፒቅ-አዳድ አሚኑምን ድል አደረገው።»
1767 ዓክልበ. - እሽመ-አሹር፣ ኤያዳን ልጅ - «ኢፒቅ-አዳድ ዚቁራቱምን ያዘ።»
1766 ዓክልበ. - አሹር-ሙታቢል፣ አዚዙም ልጅ - «ኢፒቅ-አዳድ <...> ።»
1765 ዓክልበ. - ሹ-ኒራሕ፣ አዙዛያ ልጅ
1764 ዓክልበ. - ኢዲን-አቡም - «ሲን-አቡም <...> ።»
1763 ዓክልበ. - ኢሊ-ዳን፣ አዙዋ ልጅ
1762 ዓክልበ. - አሹር-ኢሚቲ፣ ኢዲን-ኢሽታር ልጅ
1761 ዓክልበ. - ቡዚያ፣ አቢያ ልጅ
1760 ዓክልበ. - ዳዲያ፣ ሹ-ኢላብራት ልጅ - «1 ሻምሺ-አዳድ ልደት።»
1759 ዓክልበ. - ፑዙር-እሽታር፣ ኑር-ኢሊሹ ልጅ - «የጸሐይ ግርዶሽ ሆነ፤ አሚኑም ዓረፈ።»
1758 ዓክልበ. - ኢሳያ፣ ዳጋን-ማልኩም ልጅ
1757 ዓክልበ. - አቡ-ሻሊም፣ ኢሉ-አሉም ልጅ
1756 ዓክልበ. - አሹር-ረዒ፣ ኢሊ-ኤሙቂ ልጅ
1755 ዓክልበ. - ጣብ-አሹር፣ ኡዙዋ ልጅ
1754 ዓክልበ. - ሹ-ራማ፣ ኡዙዋ ልጅ
1753 ዓክልበ. - ሲን-እሽመአኒ
1752 ዓክልበ. - አሹር-ማሊክ፣ ሹ-ሃኒሽ ልጅ
1751 ዓክልበ. - ዳን-ኤያ፣ አቡ-ዋቃር ልጅ - «የሑፕሹም መያዝ»
1750 ዓክልበ. - ኤና-ሲን፣ ኢዲን-አቡም ልጅ - «ጐርፍ በሩቅ አገር»
1749 ዓክልበ. - አሹር-በላጢ
1748 ዓክልበ. - ኤና-ሲን
1747 ዓክልበ. - ኢቱር-አሹር
1746 ዓክልበ. - ሹ-በሉም - «ኢላ-ካብካቡ ሱፕሩምን ያዘ።»
1745 ዓክልበ. - ሻሩም-አዳድ፣ ቡዛዙ ልጅ - «ኤላም ሰው (ኩዱር-ማቡግ) ኢፒቅ-አዳድን አሸነፈ፤ ሻምሺ-አዳድ ያባቱን ቤት ገባ።»
1744 ዓክልበ. - ሹ-ላባን
1743 ዓክልበ. - አሹር-ኢሚቲ - «ሉሉ ንጉሡን በላዛፓቱም አሸነፉት።»
1742 ዓክልበ. - ዳዳያ - «ሙት-አቢህ <...>፤ ኢፒቅ-አዳድ አራጳን ያዘ።»
1741 ዓክልበ. - አህ-ሻሊም - «የጋሱር (ኑዚ) መያዝ»
1740 ዓክልበ. - ኡጹር-ሺ-እሽታር
1739 ዓክልበ. - ካታያ
1738 ዓክልበ. - ሹ-ሲን
1737 ዓክልበ. - አቡ-ሻሊም - «የሲን-አቡሱም ከነረብቱም መያዝ።»
1736 ዓክልበ. - ሹዳያ
1735 ዓክልበ. - ሹ-ዳዱም - «የነ<...> መያዝ።»
1734 ዓክልበ. - አሹር-ዱጉል - «ሻምሺ-አዳድ የኡኒኒ ሰው አሸነፈ፤ ሙት-ያ<...> አሸነፈ።»
1733 ዓክልበ. - ፑዙር-እሽታር - «ሻምሺ-አዳድ <...>።»
1732 ዓክልበ. - አታናህ - «ኢፒቅ-አዳድ <...> አሸነፈ፤ <...> ምድርን ያዘ።»
1731 ዓክልበ. - ኢሪሹም - «ሻምሺ-አዳድ <...>ን በዱር-<...> አሸነፈ።»
1730 ዓክልበ. - አሹር-ኤናም
ቀዳሚው
2 ፑዙር-አሹር
አሹር ገዥ
1782-1730 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
2 ኤሪሹም
  1. ^ የመስጴጦምያ ነገሥታት (ፈረንሳይኛ)
  2. ^ የሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል