2 ኢፒቅ-አዳድሱመርኤሽኑና ንጉሥ ነበረ (1771-1729 ዓክልበ. የነገሠ)። የ1 ኢባልፒኤል ተከታይ ነበረ።

የኢፒቅ-አዳድ ዘመነ መንግሥት በተለይ «ማሪ ሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል» (MEC) ከተባለው ሰነድ ሊታወቅ ይችላል።[1] እንዲሁም ከዓመት ስሞቹ መሃል ፲፬ ያህል ከሥነ ቅርስ ተገኝተዋል።[2] ከነዚህ መካከል፦

1771 ዓክልበ. - «ኢፒቅ-አዳድ ያባቱን ቤት የገባበት ዓመት» (ዓመት ስም 'a'፣ MEC)
1769 ዓክልበ. - «አሚኑም (የኡኒና ንጉሥ) ኢፒቅ-አዳድን ድል አደረገው።» (MEC)
1768 ዓክልበ. - «ኢፒቅ-አዳድ አሚኑምን ድል አደረገው።» (MEC) = «ኢፒቅ-አዳድ ኡኒናን ያሸነፈበት ዓመት»? (ዓመት ስም 'b')
1767 ዓክልበ. - «ኢፒቅ-አዳድ ዚቁራቱምን ያዘ።» (MEC)
1766 ዓክልበ. - «'ኢፒቅ-አዳድ <...> ።» (MEC)
(1755 ዓክልበ. - «የኤሽኑና ምድር የጠፋበት ዓመት» የሚባል የላርሳ ንጉሥ ሲን-ኢዲናም ዓመት ስም አለ።)
1745 ዓክልበ. - «የኤላም ሰው (ኩዱር-ማቡግ) ኢፒቅ-አዳድን አሸነፈ።» (MEC)
? - «ኢፒቅ-አዳድ ኤላማውያንን ያሸነፈበት ዓመት» (ዓመት ስም 'd')
1742 ዓክልበ. - «ኢፒቅ-አዳድ አራጳን (የጉቲዩም ዋና ከተማ) የያዘበት ዓመት» (ዓመት ስም 'ea'፤ MEC)
1741 ዓክልበ. - «ኢፒቅ-አዳድ ጋሱርን (ኑዚን) የያዘበት ዓመት» (ዓመት ስም 'eb'፤ MEC)
1737 ዓክልበ. - «የሲን-አቡሹም ከነረብቱም መያዝ።» (MEC)
1735 ዓክልበ. - «ኢፒቅ-አዳድ ነረብቱም የያዘበት ዓመት» (ዓመት ስም 'f'፤ MEC)
? - «ኢፒቅ-አዳድ ዱር-መቱራንን የያዘበት ዓመት» (ዓመት ስም 'j')
? - «ኢፒቅ-አዳድ ራፒቁምን የያዘበት ዓመት» (ዓመት ስም 'k')
? - «ኢፒቅ-አዳድ ሃላቢትን የያዘበት ዓመት» (ዓመት ስም 'm')
1732 ዓክልበ. - «ኢፒቅ-አዳድ <...> አሸነፈ፤ <...> ምድርን ያዘ።» (MEC)
1731 ዓክልበ. - «1 ሻምሺ-አዳድ <...>ን በዱር-<...> አሸነፈ።» (MEC)
1729 ዓክልበ. - «ኢፒቅ-አዳድ ዓረፈ።» (MEC)

ኢፒቅ-አዳድ ለኤሽኑና ሰፊ ግዛት ስለ ጨመረ «የኤሽኑና አስፋፊና የዓለም ንጉሥ» የሚልን ስያሜ ደፈረ።

ቀዳሚው
1 ኢባልፒኤል
ኤሽኑና ንጉሥ
1771-1729 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ናራም-ሲን

ዋቢ ምንጮች ለማስተካከል

  1. ^ የሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል 'MEC'
  2. ^ የኢፒቅ-አዳድ ዓመት ስሞች