ኒጄር ወንዝጊኔማሊኒጄርቤኒንናይጄሪያ የሚፈስስ ታላቅ ወንዝ ነው።

ኒጄር ወንዝ (ማሊ)

ይህ ምናልባት ቶለሚ የጠቀሰው ወንዝ «ኒግሪስ» ወይም «ኒጊር» ሊሆን ይችላል። በአልጄሪያ ደግሞ «ጊር» የተባለ ወንዝ እያለ፣ ከዚያና ከኒጄር ወንዝ መካከል ያለው ሀገር በጥንት «ኒግሪቲያ» ወይም «መላኖጋይቱሊያ» ይባል ነበር። ይህም ማለት «ጥቁር ጌቱሊያ» ሲሆን፣ ሕዝቦቹ ከጌቱሊያ ወይም ከኩሽ ልጅ ኤውላጥ እንደ ደረሱ ይታመን ነበር።

በሌላው ዳር ከኒጄር ወንዝ ደቡብ ያለው ሀገር በጥንት «ምዕራብ ኢትዮጵያ» ወይም «ጊኔዋ» ይባል ሲሆን ሕዝቦቹ ከኩሽ ልጅ ራዕማ እና ከርሱ ልጅ ድዳን እንደ ደረሱ ይታመን ነበር።

ወንዙም በበርበርኛ ወይም ቷሬግ ስያሜው «ጋረው-ን-ጋራዋን» ማለት የወንዞች ወንዝ በመሆኑ፣ ጥንታዊው ትርጉሙ ከዚያው ጋር እንደተዛመደ ይታስባል እንጂ ከሮማይስጡ /ኒጌር/ ጥቁር እንደ ወጣ አሁን አይታመንም። ይልቁንም ሮማይስጡ ቃል ከኒግሪቲያ ዜጎች እንደ ተወሰደ ይቻላል።