ጌቱሊያ በስሜን አፍሪካ የተገኘ ጥንታዊ አገር ነበር። ከሮማውያን መምጣት በፊት ከሜድትራኒያን ባሕር ወደ ደቡብ እስከ ሳህራ በረሃ ድረስ በዛሬው አልጄሪያ ያለውን አገር ይሸፍን ነበር። የሮሜ መንግሥት ኑሚዲያንና ማውሬታኒያንን ከያዘ በኋላ፣ ፕሊኒ እንደሚለው ጌቱሊያ ከአትላስ ተራሮች ወደ ደቡብ እስከ ኒጄር ወንዝና እስከ አይቲዮፒያ ጠረፍ ድረስ ያለውን አገር ሁሉ ጠቀለለ። የጌቱላውያን ተወላጆች ዛሬ የቤርቤር ብሔሮች ናቸው።