ኒዌ Niue በፓሲፊክ ውቅያኖስ የሚገኝ የኒው ዚላንድ ራስ-ገዥ ደሴት አገር ነው።

ኒዌ
Niuē
Niue

የኒዌ ሰንደቅ ዓላማ የኒዌ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Ko e Iki he Lagi

የኒዌመገኛ
የኒዌመገኛ
ዋና ከተማ ኣሎፌ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ኒዌኛ
እንግሊዝኛ
መንግሥት


ንግሥት

ጠቅላይ ሚኒስትር
የአንድነት ፓርለሜንታዊ ህገ መንግስታዊ ንጉሳዊ አገዛዝ (ኒው ዚላንድ ግዛት)
ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ፪ኛ
ጆን ኪይ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
18,274
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
 

1,612
ሰዓት ክልል UTC −11
የስልክ መግቢያ +683
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .nu

ደሴቱ መጀመርያ በኢንግላንድ ተጓዥ ጄምስ ኩክ1766 ዓም ተዘገበ። የክርስትና ሰባኪዎች ከ1838 ዓም ጀምሮ ደርሰው የኗሪዎቹ ብዛት የክርስትና ምዕመናን ሆነዋል። መጀመርያው ክርስቲያን ንጉሥ ቱዊ-ቶጋ ከ1867-1879 ነገሠ።

1881 ዓም የፈረንሳይ ቅኝ አገር እንዳይሆኑ ፈርተው በራሳቸው ልመና በዩናይትድ ኪንግደም ጥብቅና ሥር ገቡ፤ በ1893 ዓም ጥብቅናው ወደ ኒው ዚላንድ ተዛውሮ እስካሁን ድረስ ከኒው ዚላንድ ጋር ተባባሪነት አላቸው። ሕዝቡ ግን ምንጊዜም በተግባር ራስ ገዥ ሆነዋል።

ይፋዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ እና ኒዌኛ ናቸው፤ ብዙዎቹም ኒዌኛ ይናገራሉ። ደሴቱም 14 መንደሮች አሉበት።

ትንሽ ኮኮነትማርፓፓያ፣ ወዘተ. ለአለም ገበያ ይመረታሉ። የእጅ ሥራዎች፣ ፣ የቴምብር፣ የእግር-ኳስ መፈብረክ፣ የቱሪስም ኢንዱስትሪዎች አሉ።

ዛሬ የኒዌ ኗሪዎች ሁሉ (1600 ያህል) ኢንተርኔት አላቸው። ራግቢ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ጨዋታ ነው። ባህላዊ ጭፈራዎች አሉ።

ብዙዎቹም በግብርና ሥራ ሲገኙ፣ ለራሳቸው አበሳሰል ካሳቫጎደሬዳቦ ፍሬሙዝ፣ ፓፓያ፣ ኮኮነት፣ ኮቴሃሬ ይመርታሉ። በዋናነት የሚበላው አሣ ነው፣ እንዲሁም ሠርጣንአሳማ ይበላሉ። በምግብ አሠራሮቹ መካከል፣ «ናኔ ፒያ» ከፖሊኔዥያ አሮውሩትና ከኮኮነት የሚሠራ አጥሚት ነው።